፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA-ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች የዜጎችን ህይወት በተጨባጭ የቀየሩ መሆኑን ገለፁ።
ከንቲባዋ ለዚህ ስራ መሳካት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የላቀ ሚና እንደነበራቸው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ለአህጉሪቱ መፃኢ ዕድል የከተሞች ልማት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።
የአፍሪካ ከተሞች ልማትና ዕድገትን በፍጥነት በማሳደግ ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።

ከተሞችን፣ ምቹ ውብና ፅዱ ማድረግ የከተሞች ከንቲባዎች ዋነኛ ስራ መሆኑንም ነው ያነሱት።በዚህ ረገድ በአዲስ አበባ ሰው ተኮር ልማቶች ላይ በማተኮር የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
በኮሪደር ልማት፣በተማሪዎች ምገባ፣ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የተለያዩ ዘርፎች ላይ የተከናወኑ ስራዎች ዜጎችን በተጨባጭ ተጠቃሚ አድርገዋል ብለዋል።በእነዚህ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውንም ነው የገለፁት።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ስራ መሳካት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የላቀ ሚና ነበራቸው ብለዋል።ፎረሙ “ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












