፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 14 2016| NBC ETHIOPIA-በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች እና ልጃገረዶች የሚፈጸመው ጾታዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ከ 3 ሴቶች አንዷ አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባት አለም አቀፍ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡
በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ለመቅፍ ሀገራት የሚያስቀምጧቸው ህጎች ሚናቸው የላቀ ነው፡፡ አስገድድ መድፈር ላይ ጠንካራ እርምጃ ከሚወስዱ ሀገራት ጥቂቶቹን መረጥንላችው፡፡
ፓኪስታን

ፓኪስታን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጠንካራ ህግ ካላቸው ሀገራት መካከል ትጠቀሳለች፡፡
በዛች ሀገር የአስገድድ መድፈር ነውር ከመሆኑም ባለፈ የሀገሪቱ ህግ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድበት ወንጀል ነው፡፡ወንጀሉ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት ፍርድ የሚያደርስ ነው፡፡
በቡድን ተደራጅቶ እና ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ህፃን መድፈር በፓኪስታን የሞት ቅጣት ነው ፍርዱ፡፡ሀገሪቱ ከአስገድዶ መድፈር ጋር የተያያዙ በርካታ ወንጀሎችን ለመቅረፍ ፤ በሴቶች እና በህጻናት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶችን ፍትህን በፍጥነት እና በተቀመጠው ህግ መሰረት ለመስጠት እንዲያመች ፍርድ ቤቶቿ ልዩ ቦታ እንደሚሰየሙ ይነገርላቸዋል፡፡
የሀገሪቱ ህግ ተግበራዊ መሆን የጀመረውም ከፈረንጆቹ 1860 ጀምሮ ነው፡፡ድርጊቱ ጸያፍ ወንጀል መሆኑን በህግ ማእቀፏ ያመላከተችው ፓኪስታን ይህን የሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ ከሚወሰዱ ቅጣቶች መካከል የእጅ እና እግር መቆረጥ ብሎም ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ክፍያን ያካትታል፡፡
ሳውዲ አረቢያ

ሳውዲ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ምላሽ ለመስጠት የሸሪዓ ህግን መሰርት አድረጋለች፡፡
በሳውዲ አረቢያ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመ አንድ ግለሰብ የሚዳኘው እስር፣ግርፍ እና መኮላሸትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ቅጣቶችን በሚጣልበት የሕግ ፊት ቆሞ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2019 ብቻ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ስምንት ዜጎቿ ላይ የሞት ፍርድ ተግባራዊ እድርጋለች ሳውዲ፡፡
ግብጽ

ግብጽ ከባድ ቅጣት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ዝርዝር ውስጥ የአስገድዶ መድፈር በግንባር በቀዳሚነት ታስቀምጠዋልች፡፡
ግብጽ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በተጠረጠረ ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣትን ተግባራዊ ታደርጋለች፣ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራትን ጨምሮ፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ሴቶችን ከግል ትንኮሳ ጀምሮ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚረዱ ህጎችን አውጥቷል፡፡ ሆኖም ግን ህግን ለማስከበር ትልቅ ማነቆ የሆነው ሴቶች ጥቃቱ ሲፈጸምባቸው ወደ ሚመለከተው አካል በመሄድ ክስ አለመመስረታቸው ነው፡፡
በዚህም በፈረንጆቹ እ.ኤ.አ. በ2008 በሀገሪቱ በተደረገ ጥናት 83 በመቶው የግብፅ ሴቶች ጾታዊ ትንኮሳ ሲደርስባቸው 12በመቶ የሚሆኑት ብቻ ጉዳያቸውን ለህግ ያቀርባሉ፡፡
ሀገሪቱ ግን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት የሚያደርስ ቅጣትን በህግ ማእቀፍ ውስጥ አስቀምጣለች፡፡
ቻይና

ቻይና ሴትን በማንኛውም ሁኔታ አታሎም ይሁን በግዳጅ መድፈርን በጽኑ እስራት የምትቀጣ ሀገር ናት፡፡
በተለይ ከ14 ዓመት በታች ከሆነች ሴት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ የሀገሪቱ ከባድ ቅጣት ያርፍበታል፡፡
ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች የሆናቸው ሴቶችን መድፈር፣ በሕዝብ ፊት ሴትን መድፈር፤ በቡድን ሆኖ ጥቃቱን መፈጸም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራትን የሚያከናንብ ስለመሆኑ ህጓ ይደነግጋል፡፡
አሜሪካ

አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ንጀለኞችን ማኮላሸትን ጨምሮ የእድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ህግ አላት፡፡
እ.ኤ.አ. በ2013 በተደረገ ጥናት አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ዝቅተኛ ሪፖርት የተደረገባት ሀገር ናት፡፡
በሀገሪቱ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ጾታዊ ጥቃቶች 0.1 በመቶ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡ ይህም የህጉ ጥብቅ መሆን እንደምክንያት ይቀርባል፡፡
ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ፓኪስታን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ ወንጀለኞች ላይ ስቅላት እና ግለሰቡን በእሳት የማቃጠል እንዲሁም እድሜ ልክ እስራትን ለመወሰን የሚያስችል እድል አለው ህጋቸው፡፡
ሀገራት የሚከተሉት የህግ አተገባባር ወንጀሎች እንዲበራከቱ ብሎም እንዲቀንሱ ምክንያት ይሆናል፡፡
የሴት ልጅ መብትና ለማራጋገጥም በ2017 ከካሪቢያን እና ከመካከለኛው አሜሪካ እስከ ዮርዳኖስ እና ቱኒዚያ ያሉ ሀገራት ከዚህ ቀደም በሴቶችን ጥቃት ያስተላልፉ የነበሩትን ውሳኔ ለማስተካካል የህግ ማሻሻያ አድርገዋል፡፡
ይህም ለጉዳዩ ትልቅ አትኩሮትን መስጠታቸውን የሚያመላክት ነው፡፡እነዚህ ሀገራት በጅራፍ መግረፍ፣ ማኮላሸት እና የሞት ቅጣት ብሎም ድርጊት ፈጸሚውን በእሳት የማቃጠል ቅጣትን በህጋቸው ደንግገው ዜጎቻቸውን እንደሚታደጉ ሁሉ በኢትዮጵያ መቆሚያ ያጣውን በተለይ ለአቅመ ሄዋን ባልደረሱ ህጻናት ላይ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር ወንጀል ለመከላከል ተሞክሮን መቅሰም የሚገባት ነው፡፡












