፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 13 2016| NBC ETHIOPIA- ቻይናና ቬትናም ለ14 ዓመት የሚቆይ የንግድ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ፡፡ሁለቱ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ የባቡር መስመር በመዘርጋት የአዞ ቆዳ ንግድ የሚሳለጥበትን መመንገድ አቅጣጫቻ አስቀምተዋል ፡፡
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዥ ጂፒንግ የቬታናሙን አቻቸውን ላምን በቤጅንግ ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፤ በሁለቱ ጎረቤታሞችና ኮሚዩኒስት ሀገራት መካከል ጠንካራ ወዳጅነትን ለማስተሳሰርና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የጋራ ትብብር ማስፈለጉን መክረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በደቡባዊ ቻይና ባህር ላይ የሚታየውን የምዕራባውያን ሽኩቻ አሰመልክቶ ሁለቱ ሀገራት ውጥረቱን ለማርገብ እንደሚሰሩ ነው የተወያዩት፡፡
ቻይና ሁሌም ከጎረቤቷ ቬትናም ጋር ቀዳሚ የሆነ ወዳጅነት ያላት ሲሆን በዚህም ሁለቱ ሀገራት በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ፤ በአስተዳደር እና በብሄራዊ ጥቅም ጉዳዮች ጥልቅ ትስስር እንዲኖር ቤጂንግ እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንት ዥ ጂፒንግ ተናግረዋል፡፡ ላም በበኩላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ለቬትናም መንግስት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ቀዳሚው ሲሆን ከቻይና ጋር የሚኖረንን ወዳጅነት ጠንካራ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል ፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












