፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 13 2016| NBC ETHIOPIA-በፈረንጆቹ መስከረም 2014 የተጀመረው የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት አሁን ድረስ መቀጠሉ በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ መፍጠሩ ተገለጸ፡፡
በዚህ ጦርነት ከአዋቂዎች በተጨማሪ ህጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡እንደ ድርጅቱ መረጃ 34 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ለከፋ በሽታና ለተመጣጣኝ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡
በየመን 6 መቶ ሺህ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጎዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 120 ሺህ የሚሆኑት አደገኛ በሚባል ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ገልጿል፡፡
መንግስት በተቆጣጠራቸው በደቡባዊ የመን የሚገኙ ዜጎች መራር ሀዘን ላይ መሆናቸውን ተመድ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
የመን በሁቲ አማጽያንና ህጋዊ መንግስት ነኝ በሚለው በማሀዲ አል ማሻት መካከል የሚደረገው ጦርነት ሀገሪቱን በአረቢያ ፔንዙላ ከሚገኙ ሀገራት የመጨረሻዋ ድሀ ሀገር አድርጓታል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የመን በሰብዓዊ መብት ጥሰት በዓለም ላይ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች ሲል ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












