፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 06 2016| NBC ETHIOPIA – የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱል ሀሚድ ዲቢባህ ወታደራዊ ጥሰቶችን ለመፈጸም እና ውስጣዊ ክፍፍልን ለመፍጠር የሚሞክር ማንኛውንም ሰው መንግስታቸው እንደማይታገስ አስጠነቀቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በትሪፖሊ የወታደሮች ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡
በሊቢያ አንድነት ላይ የሚመጣ ማንኛውም አካል ቀይ መስመር እንደሚጥስ ማወቅ ይኖርበታል፤ ከፈጣሪ ጋር ሆነን ጠንካራ መከላከያ መገንባታችንን እንቀጥላለን ብለዋል ፡፡
ዲቢባህ የአባቶቻችን ፈለግ ተከትለን ከውጭ የሚመጣ አካልን በመቃወም እና አምባገነኖች ተመልስው ለመምጣት የሚያደርጉትን ሙከራ ማክሸፍ ይጠበቅብናል ሲሉ ለተመራቂ ወታደሮች መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡
ባለፈው አርብ በሊቢያ ምስራቃዊ ክፍል ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 9 ሰዎች ሲሞቱ 16 መቁሰላቸው ይታወሳል ድርጊቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዲቢባህን አስቆጥቷል፡፡
ይህን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጊቱን በማውገዝ የሀገሪቱ ወታደራዊ ሀይሎችና የድህንነት አባላት በጋራ ህጋዊና ተጠያቂ የሆነ ተቋም መመስረት ይጠበቅባቸዋል ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡
ሊቢያ የቀድሞው መሪዋ ሙዓመር ጋዳፊ በፈረንጆቹ 2011 ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ፤የፖለቲካ አለመረጋጋት የሚታይባት ሀገር ሆና መቀጠሏን ያስነበበው ሲ. ጅ. ቲ ኤን ነው ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












