፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 03 2016| NBC ETHIOPIA-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ክረምት ገፀ በረከት ነው በክረምት ሁሉም ነገር የተፈጥሮን ውብ ዜማ ይከተላል ምድሩ በአረንጓዴ ቀለም ይሞሸራል ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋራቱ መልዕክት እኛም በተፈጥሮ ዜማ እና በምድር መልክ ስልት ገፀ በረከት ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ሀገር ለማስረከብ አሻራችንን እናኖራለን፡፡

ዛሬ ከስደተኞች ተመላሾች አገልግሎት የስራ ሃላፊዎች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሂደናል፡፡ ሀገራችንን አረንጓዴ የማልበስ ዘመቻችንን በትጋት እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












