፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 03 2016| NBC ETHIOPIA- ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መካሄድ መጀመሩን ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለል እና ከተማችንን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በ2016 በጀት ዓመት ከያዝነው አጠቃላይ እቅድ በአማካይ ከ91% በላይ የሚሆነውን ማሳካት ችለናል ብለዋል፡፡ ይህም አዲስ የስራ ባህል በመተግበር ያሳካነው ነው ሲሉ አመልክተዋል።

በግምገማችንም በ2016 በጀት ዓመት ስኬቶቻችንን በማላቅና በማስፋፋት፣ የጥንካሬዎቻችንን ምንጭ በመለየት እንዲሁም ጉድለቶቻችንን በመሙላት እና በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለኑሮ የተመቸች ውብ አበባ የሆነች ከተማ ለመገንባት የጀመርነውን ስራ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












