፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 02 2016| NBC ETHIOPIA-
በሰሜን ሽዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ሬማ-ንዑስ ወረዳ ሬማ ከተማ በክልሉ ተፈጥሮ የነበረዉን የሰላም ችግር ለመፍታት ያለመ የህዝብ የሰላም ኮንፍረስ ተካሄደ::
በውይይቱ የተገኙት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ሰላም ወዳዱ የወረዳችን ህዝብ በተፈጠረዉ ወቅታዊ የሰላም ችግር ምክንያት ለዘርፉ ብዙ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች መዳረጉን የገለፁ ሲሆን ”የሰላም መጥፎ የሁከት መልካም የለምና” ሁላችንም የገጠመንን የፀጥታ ችግር ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ መትጋት አለብን ብለዋል::

ውይይቱን የመሩት የ83ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮ/ልብ ሲሳይ ፍፋ, የ101ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር ምን/ል አዛዥ ለኦብሬሽናል ማቴዮስ ማዴቦ ,የወረዳዉ ም/ል አስተዳዳሪ አቶ አባይነዉ ወንደሰን እና ሌሎች የፀጥታና የወረዳ አመራሮች የመሩት ሲሆን በክልሉ የተፈጠረዉ የፀጥታ ችግር በልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ ከፋተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ከማሳደሩም በላይ የወረዳዉን ብሎም የክልሉን ህዝብ ለከፋ ድህነትና እንግልት የዳረገ በመሆኑን ገልፀዋል::

በመጨረሻም ሰላም ለሰዉ ልጆች የህልዉና ጉዳይ መሆኑን ተረድተን ሁላችንም የአካባባያችንን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ የበኩላችንን መወጣት እንደሚያስፈልግ በመጠቆም ዉይይቱ መጠናቀቁን የአማራ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል ::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












