፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 01 2016| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የመዝናኛ እና የዕምነት ተቋማት እንዲሁም ተሽከርካሪዎች በከተማዋ የአብዛኛው የድምፅ ከብክለት ምንጭ ስለመሆናቸው ተገልጿል።
ከሚቀርቡለት ቅሬታዎች አብዛኛው የድምፅ ብክለት ላይ ስለመሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በእዚህም መሰረት ባለፉት በሶስት ወራት 2190 ተቋማት ከማስጠንቀቂያ እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

እርምጃ ከመውሰድ ባሻገርም ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል ተብሏል።ባለስልጣኑ ከእቅዱ አንጻር 95.6 በመቶ ማሳካት እንደቻለ አስታውቋል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












