፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 01 2016| NBC ETHIOPIA-የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶመር ባርላቪ ጋር በቱሪዝም፣ የእህትማማች ከተሞችን ለማጠናከር እና የልማት እንቅስቃሴዎችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርጓል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ጋር በቱሪዝም ዘርፍ፣ በሌሎች የልማት የሥራ እንቅስቃሴዎችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

ምክክሩ ጎንደር ከተማ እስራኤል ካሉ እህት ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሕዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት ዋና አማካሪ ቻላቸው ዳኘው እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ የመሠረተ ልማት ዋና ሥራ አሥኪያጅ አንዱዓለም ሙሉ መሳተፋቸውን ከጎንደር ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












