፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 30 2016| NBC ETHIOPIA-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የነሀሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን ገለፁ::
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ትዕዛዙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል::
በየደረጃው የሚገኝ የንግድ መዋቅር በነዳጅ ስርጭትና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ስራዎች መጀመራቸውን አስታውቀዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












