፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 29 2016| NBC ETHIOPIA- የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ የተካረረው ውጥረት ለድፍን ቀጠናው የሚተርፍ ጦርነትን ያመጣል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በሀብት የበለፀጉትና ቡድን ሰባት በሚል የሚታወቁት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ባወጡት መግለጫ በመካከለኛው ምስራቅ አሁን ያለው ውጥረት ወደከፋና ግዙፍ ጦርነት የሚያመራ ከሆነ ከዚያ ቀጠና ባለፈም ለሌሎች የሚተርፍ አደጋ አለው ሲሉ ነው ያስጠነቀቁት።
የካናዳ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ጃፓን ፣ እንግሊዝ ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ተወካይ በጋራ ባወጡት መግለጫቸው አሁን በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ያለው ውጥረት ለማንም ትርፍ የሌለውና እልቂት የሚመዘገብበት ነው ሲሉ የቀጠናው ሀገራት ከዚያ ደረጃ ላይ ላለመድረስ ቆም ብለው ያጤኑት ዘንድም ነው ያሳሰቡት ዘገባው የአናዶሉ ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












