፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ዓለማችን በታሪኳ ካየቻቸው የቅርጫት ኳስ ከዋክብት መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ከስፖርቱ ዓለም ስኬቱ ባሻገር በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች የሚያደርጋቸው አነቃቂ ንግግሮች ተወዳጅነትን ከማፍራት ባሻገር ለበርካታ የዓለማችን ወጣቶች አርዓያ ሆኗል ። ተፅዕኖው ከቅርጫት ኳስ አፍቃሪዎች ባሻገር በሌሎች ስፖርተኞችና ከስፖርቱ ዓለም ውጪ ባሉ ወጣቶች ላይ ማረፍ ችሏል።ኮቢ ብራይንት!

የተወለደው እ.ኤ.አ በ1978 በአሜሪካዋ ፊላዴልፊያ ሲሆን የወላጅ አባቱን ጆኢ ብራይንትን ፈለግ በመከተል ኮቢ ብራያንት ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመረው በልጅነት እድሜው ነበር፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ፣ ኮቤ እ.ኤ.አ በ1996 የልጅነት ህልሙ የነበረውን ‘’ሌከርስ” የቅርጫት ኳስ ቡድንን በመቀላለቀል የቅርጫት ኳስ ህይወቱን አሃዱ አለ፡፡ አስርት ዓመታትን በቡድኑ ያሳለፈው ኮቢ ባሳየው ድንቅ ብቃት እውቅናን እና ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡
በ20 ዓመታት የቅርጫት ኳስ ፕሮፌሽናል ህይወቱ አያሌ ክብሮችን የጨበጠው ኮቢ ሁለት ጊዜ የአሜሪካ ኦሊምፒክ ቡድኖች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆን የቻለ ሲሆን በ 2008 በመድረኩ ውዱ ተጫዋች መሆን ከመቻሉም በተጨማሪ 2006 ላይ ከቶሮንቶ ራፕቶርስ ጋር በገጠመበት ጨዋታ 81 ግቦችን በማስቆጠር 2ኛው የምንጊዜም ከፍተኛ ቅርጫት አስቆጣሪ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል።

የ18 ጊዜ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ መመረጥ የቻለ ሲሆን ለአምስት ጊዜ የኤን ቢ ኤ ቻምፒዮን በመሆንም በቅርጫት ኳስ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ማትረፍ ችሏል። እ.ኤ.አ በ2017 በኮቢ ብራያንት ተደርሶ በ በግሌን ኪን ዳይሬክት የተደረገው Dear Basketball የተሰኘው የአንሜሽን ፊልም በ 2018 የኦስካር ሽልማት አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬትን የተጎናጸፋት የቅርጫት ኳስ ህይወቱ እውቅናን እና ስኬትን ያተረፈበት ብቻ ሳይሆን በውድድር ዘመኑ በጉልበቱ እና በትከሻው ላይ የደረሰ የጡንቻ ከባድ ጉዳትም እንዲያስተናግድ ምክንያት ሆኗል፡፡ ጉዳቶቹን ለአመታት ተቋቁሞ በቅርጫት ኳስ ዓለም ታላቅ ታሪክ መስራት የቻለው ኮቢ እ.ኤ.አ 2016 የውድድር ዘመን ጡረታ መውጣቱን በይፋ አስታውቋል፡፡ ከክለቡ አባላት ሲለያይም ይህንን አይረሴ ንግግር አድርጎ ነበር፡፡

የሀብት መጠኑ 650 ሚሊየን ዶላር እንደሚደርስ የሚገመተው ኮቢ በ2001 ዓ.ም ከቫኔሳ ብራያንት ጋር በትዳር በመጣመር 4 ልጆችን ማፍራት ችሏዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት በአያሌ ልፋቶች እና ጥረቶች ያለፈው ኮቢ የቅርጫት ኳስ ጫዋታ ለእርሱ ዓለምን የሚመለከትበት መነጸሩ እንደሆነ ይናገራል፡፡
ለበርካታ የዓለማችን ከዋክብት ስፖርተኞች የአሸናፊነትና ጥሩ ምግባር አርዓያ የሆነው ኮከብ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብራያንት ከ4ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ2020 የሴት ልጁን
የቅርጫት ኳስ ቡድንን ለማሰልጠን ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል ሲጓዝ በካሊፎርንያ በደረሰው ድንገተኛ የሄልኮፕተር መከስከስ አደጋ በ41 ዓመቱ ሕይወቱ የማለፉ አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል፡፡ ክስተቱን አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ በአደጋው የ13 ዓመቷ የኮቢ ብራያንት ልጅ ጂያና ብራያንት ከአባቷ ጋር ህይወቷ ማለፉ ነው።

የሀብት መጠኑ 650 ሚሊየን ዶላር እንደሚደርስ የሚገመተው ኮቢ በ2001 ዓ.ም ከቫኔሳ ብራያንት ጋር በትዳር በመጣመር 4 ልጆችን ማፍራት ችሏዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት በአያሌ ልፋቶች እና ጥረቶች ያለፈው ኮቢ የቅርጫት ኳስ ጫዋታ ለእርሱ ዓለምን የሚመለከትበት መነጸሩ እንደሆነ ይናገራል፡፡
ለበርካታ የዓለማችን ከዋክብት ስፖርተኞች የአሸናፊነትና ጥሩ ምግባር አርዓያ የሆነው ኮከብ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብራያንት ከ4ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ2020 የሴት ልጁን የቅርጫት ኳስ ቡድንን ለማሰልጠን ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል ሲጓዝ በካሊፎርንያ በደረሰው ድንገተኛ የሄልኮፕተር መከስከስ አደጋ በ41 ዓመቱ ሕይወቱ የማለፉ አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል፡፡ ክስተቱን አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ በአደጋው የ13 ዓመቷ የኮቢ ብራያንት ልጅ ጂያና ብራያንት ከአባቷ ጋር ህይወቷ ማለፉ ነው።
በወቅቱ የ 13 ዓመቷ ታዳጊ ጂያና ለመምባ ስፖርትስ አካዳሚ እየተጫወተች የነበረ ሲሆን በታሪካዊው የቅርጫት ኳስ ባለሟል በሆነው አባቷ ያሰለጥናት እንደነበር ግለታሪካቸው ያወሳል፡፡በአደጋው ኮቢ ብራይንት ጨምሮ ሌሎች ሰባት ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል። ክስተቱም በቅርጫት ኮስ አፍቃሪያን ብሎም መላው ዓለምን ያሳዘነ ነበር፡፡ ከህልፈተ ህይወቱ በኋላ ታዋቂ ግለሰቦች በስሙ በርካታ ነገሮችን ሰይመዋል፡፡
ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ጁኒየር ከሊል ጋር በተደረገው ጨዋታ 2 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን 2ኛውን ጎል መታሰቢያነቱ ለኮቢ ብራያንት አድርጓል። ተጫዋቹም የኮቢ ብራያንትን መለያ የሆነውን ምልክት ግቡን ካስቆጠረ በኋላ ለዓለም ህዝብ አሳይቷል፡፡
የአይበጌሬ እና የጽናት ተምሳሌቱ ኮቢ ብራይንት ምንም እንኳን በአሳዛኝ ክስተት ህይወቱ ብታልፍም በተለያየ መድረኮች ከራሱ የህይወት ልምድ በመነሳት ያደረጋቸው አነቃቂ ንግግሮች ለብዙዎች የመንፈስ ስንቅ ሆኖ ቀጥሏል፡፡












