፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በአሁን ወቅት ሰዎች መረጃዎችን ፣ የተለያዩ ትምህርታዊ ፣ አዝናኝ እና የተለያየ ዘውግ ያላቸው ቪዲዮዎችን ለማግኘት ወደ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ጎራ ይላሉ ፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በርካታ እያታን እያገኙ ከመጡ ዘውጎች ውስጥ ደግሞ ፖድ ካስት ተጠቃሽ ነው ፡፡
ፖድ ካስት አዘጋጆቹ አንድ ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎችን በመጋበዝ ስለ ግል ታሪካቸው እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ነጻነት የተሞላበት ውይይትን የሚያደርጉበት ነው ፡፡
ለዛሬ አለም አቅፍ ተቀባይነትን ካገኙ እና በርካታ ተከታዮች ካሏቸው ፖድካስቶች ጥቂቶቹን ልንነግራቹ ወደድን ፡፡
1.Joe Rogan Experience

ዛሬ ላይ በአለማችን ከፍተኛ ተቀባይነት ካሏቸው ፖድካስት በቀዳሚነት ስሙ ይነሳል በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁት የJoe Rogan Experience ፖድካስት ፡፡ እ.አ.አ በ2009 በታዋቂው አሜሪካዊ ኮሜዲያን Joe Rogan በዩቲዩብ የተጀመረው ይህ ፖድካስት በአጭር ግዜ ውስጥ በመላው አለም ከፍተኛ ተቀባይነትን እና ተከታዮችን ማፍራት ችሏል ፡፡አስርት አመታትን ባስቆጠረው የፖድካስቱ ቆይታ ከ2ሺ በላይ ክፍሎችን ለአድማጭ ተመልካቶች በYouTube እና Spotify ማድረስ ችሏል ፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃም 17 ሚሊየን የዩቲዩብ ተከታዮችን አፍርቷል ፡፡
ከሁለት እስከ ሶስት ሰአት ቆይታ ባለው አስተማሪ እና አዝናኝ ፖድካስት ዝነኛ አርቲስቶች ፣ጸህፊያን፣ ተጽኖ ፈጣሪሰዎች እየተገኙ ሃሳባቸውን እና ልምዳቸውን ያካፍላሉ ፡፡በ2018 ከታዋቂው ባለሀብት የቴስላ እና የቀድሞው ቲዊተር ባለቤት Elon Musk ጋር ያደረገው ቆይታ በዩቲዩብ ከ68 ሚሊዮን በላይ እይታን በማግኘት ቀዳሚው ፣መሆን ችሏል ፡፡Mike Tyson ፣ Kanye West ፣ Bernie Sanders እና Kevin Hart በፖድካስቱ ላይ ከቀረቡ ታዋቂ ሰዎች መካከል ይገኙበታል፡፡
2.Tucker Carlson

በፖለቲካ ጉዳዮቹ የሚታወቀው ታዋቂው አሜሪካዊ ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ tucker Carlson በዩቲዩብ የሚያዘጋጀው ፖድ ካስት የብዙዎችን ቀልብ ከሳቡ ፖድካስቶች አንዱ ነው፡፡
ወቅታዊ ጉዳዮች አለም አቀፍ የፖለቲካ ትንታኔዎች እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥነው ይህ ዝግጅት የሀገር መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች የሚሳተፉበት ነው ፡፡
በቅርቡም አለም በጉጉት ጠብቆ የተመለከተው ከራሺያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረገው ቃለመጠየቅ ተጠቃሽ ነው ፡፡ ይህም ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ጦርነት ከገቡ በኋላ ፑቲንን ኢንተርቪው ያደረገ የመጀመሪያው የምዕራብ ጋዜጠኛ ያደርገዋል ፡፡
3.Jay Shetty podcast

በJ ay Shetty የሚዘጋጀው Jay Shetty podcast ሌላኛው በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ፖድካት ነው ፡፡ በ2019 የተጀመረው ይህ ፖድካስት በመጀመሪያው አመት ብቻ 64 ሚሊዮን ግዜ ሰዎች ከዩቲዩብ ላይ አውርደው ተመልክተውታል፡፡
Jay Shetty በይበልጥ በአይምሮ ጤንነት ዙሪ ያተኮሩ ወይይቶችን በማድረግ ይታወቃል ፡፡2023ም በኋይት ሃውስ በተቀረጸው ምእራፉ ላይ በአሁን ወቅት በአይምሮ ጤንነታቸው ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ጆ ባደንን የአእምሮ ጤንነታቸውን በተመለከተ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል ፡፡
Jay Shetty ፖድ ካስት የአለም ምርጡ የጤና ፖድካስት በማለት Forbes አስነብቧል ፡፡ ሌሎች በርካታ ሽልማቶች እና እውቅናዎችንም በተለያዩ ጊዜያት አጊኝቶል ፡፡ በአሁን ወቅት በዩቲዩብ ብቻ 4.7 ሚሊዮን ተከታዮች እና በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች 50 ሚሊዮን ከተታዮችን ማፍራት ችሏል ፡፡
4. Valuetainment

በዋነኛነት በቢዘነስ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ሰዎች ሕልሞቻቸውን እንዲያሳኩ በማነሳሳት እና የድርጅትና የግል እድገት መሠረታዊ ነገሮች በማስተማር በአሁን ወቅት በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነት እያገኙ ከመጡ ትምህረት ሰጪ ፖድካስቶች መካከል Valuetainment አንዱ ነው ፡፡ በፓትሪክ ዴቪድ የተጀመረው ፖድካስት አምስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን አለም አቀፍ ተከታዮችም አሉት ፡፡
በሀገራችንም ዘርፉ ብዙ ተሰርቶበታል ማለት ባይቻልም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ፖድካስቶች እየተጀመሩ ነው ፡፡ ቢዝነስ፣መዝናኛ እና መሰል ቁምነገር አዘል ፖድካስቶች ብቃ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡












