፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 23 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በባህር ዳር ከተማ በከፍተኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ጉዳት በተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን አስታወቀ ፡፡
ትላንት ምሽት 1፡00 ጀምሮ ከባህር ዳር ቁ.2 የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በተዘረጋ 15 ኪ.ቮ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ኬብል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
በጉዳቱም በአየርሀይል፣ በመኮድ፣ በአየር መንገድ፣ በውሃ ጉድጓዶች፣ በቀበሌ 14 እና 16 ባሉ ፋብሪካዎች፣ በቀበሌ 13፣ 14 እና 16 እንዲሁም በአሚኮ፣ በወገልሳ፣ በዘጌ፣ በላታ፣ በጭንባ፣ በከይባብ፣ በመራዊና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጧል።
የተቋረጠውን አቅርቦት ለመመለስ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንና ነዋሪዎችም በትግስት እንዲጠብቁ የኢትዮያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠይቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












