፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የምንጊዜም ተወዳጅ እና ትልቅ ተፅዕኖን መፍጠር ከቻሉ የካርቶን ፊልሞች መካከል ቀዳሚው ነው:: ዛሬ በዓለማችን የተከሰቱ አነጋጋሪ ሁነቶችን ከዓመታት በፊት ቀድሞ የተነበየ የፊልም ነብይ ነውም ይባልለታል፡፡ዘ ሲምፕሰን
ዘ ሲምፕሰን የአሜሪካዊው ማቲ ኤብርሃም ሮኒነግ የፈጠራ ውጤት ሲሆን በፎክስ ብሮድካስቲነግ ካምፓኒ የሚተላለፍ አስቂኝ ተከታታይ የካርቶን ሲትኮም ነው፡፡
እንደ አውሮፓውያነኑ አቆጣጠር በ1987 ትሬሲ ኡልማን ሾው ላይ በአጭር ደቂቃ ይሄድ የነበረው ሲትኮም ተወዳጅነቱ ከፍ እያለ ሲመጣ በ1989 ግማሽ ሰአት ተመድቦለት መተላለፍ ጀመረ ፤በመቀጠልም በ 1990 በፎክስ ቴሌቪዥን ተላልፎ በርካቶች ተከታትለውታል፡፡

Matt Groening has revealed the location of the real-life home of The Simpsons.
ይህ የካርቶን ፊልም በዋነኝነት 6 ገጸ ባህሪያት ያሉት ሲሆን ሌሎች በርካታ ገጸ ባህሪያት በየጊዜው ተካተው ተውነውበታል፡፡ በዋነኝነት በቤተሰቡ ውስጥ የሚያስመለክተው ሁነት የብዙዎችን የቤት ውስጥ ባህሪ እና አኗኗር በሚዳስስ መልኩ የሚቀርበው ይህ አስቂኝ የካርቶን ሲትኮም በጅማሮው ወቅት እምብዛም ተቀባይነት ባያገኝም ቀስ በቀስ ተወዳጅነቱ እየጨመረ መሄድ ችሏል፡፡
በ768 ትዕይንቶች በምዕራፎች ተከፋፍሎ የቀረበ ረዥሙ ተከታታይ የአሜሪካን ሲትኮም ነው፤
ሲምፕሰን ተከታታይ ሲትኮም ከማሳቅ፤ ከማዝናናት፤ እና የብዙ አሜሪካውያን የቤተሰብ ህይወት ከመግለጡ ባለፈ እስከዛሬ ድረስ የሚነገርላቸው በፊልሞቹ ሲኖች ላይ ገጸ ባሪያቱ የተናሩት ንግግር፤ የለበሱት አለባበስ ፤ የሚጠቀሙበት የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ጭምር በወቅቱ ያልነበሩ እና ከጊዜያት በኋላ ግን እውን ሆነው በርካቶችን ያስደነቁ ናቸው፡፡
ከሰሞኑ አለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ዳግም የዚሁ ድራማ ሲኖች በስፋት መነሳታቸውን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ያላሳየናችሁን ቀሪ የፊልሙ ትንበያዎች መካከል ቀሪዎቹን እናሰቃኛችኋለን፡፡
በስፕሪንግ ፊልድ በአንድ ህጋዊ ቁማር መጫወቻ ስፍራ ሁለት የአስማት ትዕይንቶችን ከዱር እንስሳ ጋር የሚያሳዩትን ሁነት ለመመልከት በርካቶች ወደ አዳራሹ ሲተሙ ይታያል፡፡
Spring field or how I learned to stop worrying and love legalizede gambling በተሰኘው የሲምፐሰን ክፍል ላይ በመድረኩ ከዱር እንስሳት ጋር ትዕይንትን ለማሳየት በመድረኩ በተሰየሙ ሁለት ሰዎች ላይ የዱር ነብሩ ጥቃት ሲያደርስባቸው ያስመለክታል፡፡
የድራማው ሲትኮም ከተለቀቀ ከጥቂት አመታት በኋላ በፈረንጆቹ 2003 ሮይ ሆርንስ የተሰኘ ግለሰብ ከነጩ ነብር ጋር በመሆን በላስቬጋስ መድረክ ላይ ትርኢት እያሳ ባለበት ሰአት ነብሩ በአንገቱ ላይ እንዲሁም በሌሎች የሰውነት ክፍሎቹ ጉዳት አድርሰውበታል፡፡

ከተሳኩ የሲምፕሰን ትንበያዎች መካከል በተለይም በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ትንበያዎች በድራማ ክፍሎቹ ታይተዋል፡፡
ከእነዛም መካከል ሁነቱ ከመከሰቱ ቀደም ብሎ በ2012 በተሰራው በምዕራፍ 23 politically inept, with homer simpson የሚል ርዕስ ተሰጥቶት በተሰራው ክፍል ላይ የካርቶን ፊልሙ ዋና ገጸባህሪ ሆመር ጄ ሲምሰን ከሌሎች የፊልሙ ገጸ ባህሪያት ጋር በመሆን ግሪክ ስለገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ ሲያብራሩ ይታያል፡፡
የሲትኮሙ ክፍል ከተለቀቀ ከ3 አመታት በኋላ ግሪክ በታሪኳ ከባድ የተባለውን የኦኮኖሚ ቀውስ ማስተናገዷ ይታወሳል፡፡ሁነቱን ተከትሎ እንደቀደመው ሁሉ በርካቶች መለስ ብለው የድራማውን ክፍል በመዳሰስ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲያሰራጩትም ተስተውሏል፡፡
በሲምሰን ተከታታይ ሲትኮም ከተተነበዩት መካከል አንዱ የ2020 የአሜሪካን ምርጫ ነው፡፡በምዕራፍ 32 ክፍል 4 በተሰራው ፊልም ላይ እርስ በእርስ ግጭት በከተማው ላይ ሰፍኖ ትራምፕ የተባለውን የፖሊቲካ ሰው የሚደግፉ ግለሰቦች በይበልጥ አካባቢውን ሲወድሙ ይታያል፡፡
በተመሳሳይ ይህ የሲምሰን ክፍል ከተለቀቀ ከአመታት በኋላ፤ በ2020 የአሜሪካ ምርጫ ጆባይደን ምርጫውን ማሸነፋቸውን እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል ማለታቸውን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሂል በመግባት ከፍተኛ ሽብርን ሲፈጥሩ ተስተውለዋል፡፡

በዓለማችን በቅርብ ጊዜያት የሚከሰቱ እንዲሁም ከዚህ ቀደም የተከሰቱ በርካታ ትንበያዎችን የተመለከቱ ሁሉ ሲምሰን ያልተነበየው ሁነት የለም ለማለት ይገደዳሉ፡፡ታዲያ አንዳንዶቹ የእውነት ከዚህ ቀደም ባሉ የፊልም ክፍሎች አሁን ላይ ካለው ሁነት በተመሳሳይ ሲከሰቱ አንዳንዴም ሲምሰን ብሎ ነበር ብቻ ለማለት የተሰሩ አሳሳች ትዕይንቶችም ይስተዋላሉ፡፡
ከሰሞኑ የአለምን ቀልብ የገዛው የአሜሪካ ምርጫ ፕሬዘዳንት ጆባይደን እራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸውን ተከትሎ በርሳቸው ምትክ ሊተኩ ይችላሉ ተብለው የሚጠበቁትን ምክትላቸውን ካማላ ሃሪስ አስመልክቶ በርካቶች የሲምሰንን ቀደመ ክፍል ለመቃኘት ሲጣደፉ ተስተውለዋል፡፡
የአለም አቀፍ ትልልቅ የዜና አውታሮች ሲኤንኤን ጨምሮ ከዚህ ቀደም በ2000 በመጋቢት ለእይታ የበቃውን “Bart to the Future,” የተሰኘውን የሲትኮሙን ክፍል በማንሳት ቀጣይ የአሜሪካን መሪ ካማላ ሃሪስ ሊሆኑ ይችላሉ እያሉ ይገኛሉ፡፡

በዚሁ የፊልም ክፍል ላይ ሊዛ የተሰኘች የመጀመሪያዋ የአሜሪካን ሴት ፕሬዘዳንት መሆንን የምትሻ ገጸባህሪ በኋይት ሀውስ ውስጥ ተቀምጣ የምታወራቸው ሁነቶች፤ የለበሰችው ወይነጠጅ አልባሳት ሳይቀር ፕሬዘዳነት ካማላ ሀሪስ ለብሰው መታየታቸው ደግሞ ይበልጥ ሰዎች እንቀደሙት ሁነቶች ሁሉ መጪውን የአሜሪካ ፕሬዝዳነት ፊልሙ ተንብየዋል ብለው እንዲያምኑም አስገድደዋቸዋል፡፡
የብዙዎች የልጅነት ትዝታና አስቂኝ እንዲሁም የፊልም ነብይ ተብሎ የተሰየመው ይህ ሲትኮም እውነት እንደዚህ ቀደሙ ትንበያው ተሳክቶለት ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዘዳንት ይሆኑ ይሆን የሚለውን የህዳሩ ምርጫ ምላሽ ይሰጠናል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












