፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዳማ| ሐምሌ 22 2016| NBC ETHIOPIA-የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ እንዲሁም የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመን የሚረዳ ምክክር ከወጣቶች ጋር እያከናወነ ይገኛል። “የዜጎችን ክብር እና ደህንነት ያረጋገጠ ጉዞ” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ምክክር ከመላው ሀገሪቷ የተወጣጡ ወጣቶች ታድመዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን፣ የመንገድ ደህንነት እና ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አባሶ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በምክክሩ ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ በምታደርገው ጥረቶች የትራንስፖርት ዘርፉ አይተኬ ሚና እንዳለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ወጣት አምራች የሰው ሀይል ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የሚይዙት በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች የተለያዩ ጥንቃቄዎችን በማድረግ እራሳቸውንም ሆነ ህብረተሰቡን ከትራፊክ አዳጋ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የስርቆት ወንጀሎች እንዲሁም ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰቱ ወጣቱ ጥቆማ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ከመላው ሀገሪቷ ከተወጣጡ ሴቶችና ወጣቶች ጋር ሲያከናውን የነበረው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












