፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 19 2016| NBC ETHIOPIA- በፈረንሳይ የባቡር ትራንፖርት አገልግሎት የብይነ መረብ መስተጓጎል እንዳጋጠመው ባለሰልጣናት አስታወቁ፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ስርዓቱን የሚያውኩ ጥቃቶች ሆን ተብለው መፈጸማቸውን የሀገሪቱ የባቡር ትራንስፖርት ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
የፓሪስ ኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ሊከበር ጥቂት ሰአታት ሲቀሩ ድርጊቱ መከናወኑ ተንኮል አዘል ጥቃት ያለበት ነው ሲሉ ባለሰልጣናቱ ጥቃቱን አውግዘዋል፡፡
በመላው ፈረንሳይ በባቡር እንቅስቃሴ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ የባቡር ትራንስፖርት ባለሰልጣናት ግምታቸውን አስቀምጠዋል ፡፡
ከዚህ ድርጊት በኋላ በመላው ፈረንሳይ የፈጣን ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የተሰረዘ ሲሆን ጉዳዩ በሀገሬው ህዝብ ዘንድ ድንጋጤን ፈጥራል ተብሏል፡፡
ለጥቃቱ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል የለም፡፡ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩን እያጣራ እንደሆነ ገልጿል፡፡
ዛሬ ምሽት በሚጀምርው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ከ8 ሺህ በላይ የዓለም አትሌቶችን ጨምሮ ሚሊዮኖች እንደሚታደሙበት ይጠበቃል ፡፡ ዘገባው የሲቢ. ኤስ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












