፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 17 2016| NBC ETHIOPIA-የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ከኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ በ2016 ዓ.ም ኦቻ በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ የነበረውን አፈጻጸም የገመገምንበት እንደነበር እና በቀጣይ አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገራቸው ነው የገለጹት።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ፖል ሃንድሊ ኦቻ ባለፈው ዓመት አማራ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ሰብዓዊ ድጋፍ አድርጓል ያሉት ዳይሬክተሩ ድርቅ እና መሰል ችግሮችን ተከትሎ ለሚፈጠር ሰብዓዊ ቀውስ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት ስለማድረጋቸውም ነው ያስረዱት።
በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር ከተፈታ በክልሉ ዘላቂ ልማት ላይ አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ዝግጅት ይደረጋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












