፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የቻይናው ፕሬዚዳንት ትናንት በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው በሀይል ዘርፍ ከሩሲያ ጋር የበለጠ ትብብሯን ወደ ላቀ ደረጃ እንደምታደርስና በኢንዱስትሪው ዘርፍም የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማስፋት ቆርጦ መቆሟን አስታውቀዋል፡፡
እንደ ቻይናው ፕሬዚዳንት ሰፊ ማብራሪያ ሁለቱ ሀገራት ለዓለም የሚበጅ ጤናማ የሀይል አጠቃቀም ለመተግበር ያለማቋረጥ በፅናት እንደሚሰሩም ነው በአፅንዖት የተገለጹት፡፡
ቻይናና ሩሲያ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን ሰባ አምስተኛ ዓመት በዚህ በተያዘው የአውሮፓውያኑ 2024 ዘመን ያከብራሉ ዘገባው የፒፕልስ ዴይሊ ኦንላይን ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












