፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 16 2016| NBC ETHIOPIA- ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትናንት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡
ፓርቲው በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
ፓርቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












