፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 15 2016| NBC ETHIOPIA-የእስራኤል ጦር በምስራቃዊ ካን ዩኒስ እና ደቡባዊ ጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላለፈ ፡፡
በምስራቅ ካየን ዩኒስ አካባቢ በስፋት ወታደራዊ ዘመቻ እና የሮኬት ጥቃት የሚደረግበት አደገኛ ስፍራ በመሆኑ ማንኛውም ነዋሪ ለቆ መውጣት እንዳለበት የእስራኤል ጦር አፈ ቀላጤ አቪቻይ አድራኢ አስታውቀዋል ፡፡
አድራኢ አክለውም ሰብአዊ እርዳታ እንዲዳረስ ወደ ተዘጋጀላቸው አል ማዋሲ ወደሚባለው ስፍራ መሄድ ግድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ቦታዎች ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ከየትኛውም ጥቃት ነጻ እንዲደረጉ ከዚህ በፊት በረጂ ድርጅቶች የወጣውን ስምምነት የሚጥስ ነው ተብሏል፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት የእስራኤል ጦር ከጥቃት ነጻ በሆነው አል ማዋሲ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ 90 ሰዎችን ገድሎ 300 የሚደርሱ ማቁሰሉ ይታወሳል ፡፡ዘገባው የአናዱሎ ነው፡፡
በ- ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












