፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 13 2016| NBC ETHIOPIA- በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት እጅን በአፍ የሚያስጭኑ አለፍ ሲልም ይህም አለ እንዴ የሚያስብሉ አዳዲስ እና አስገራሚ ጉዳዮችን ይከሰታሉ ለዛሬም በዚህ ሳምንት በአለም ዙሪያ አስገራሚ ሆነው ያለፉ ጉዳዮችን እናስቃኛችሁ፡፡
በመጀመሪያ የመረጥንላችው አስገራሚ ጉዳይ ወደ ዋሽንግትን ይወስደናል
የትራፊክ መጨናናቅ ጎልቶ በሚታይባቸው ሰዓታት ዋሽንግትን ጨምሮ በበለጸጉት ሀገራት ከተሞች ተግባራዊ የሚደርግ የኤች ኦ ቪ መስመር ህግ አለ፡፡
ህጉም ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በሚኖርበት ሰዓት የግል ተሽከርካሪዎች 2 እና ከዚያ በላይ ሰው ካሳፈሩ ከትራፊክ መጨናነቅ ውጭ የሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ የሚያደርግ አሰራር ነው፡፡ አንዳንድ ከተሞች ይህን መንገድ ለመጠቀም ክፍያም ይጠይቃሉ፡
በዋሽንግተን ለዚሁ ዓላማ የሚውል የኤች ኦ ቪ መንገድ ላይ በፍጥነት በማሽከርከሯ የተከሰሰች ሹፌር መንገዱን ለመጠቀም የፈጠረችወ ዘዴ ግርምት ጫሪ ሆኗል፡፡
ጉድና ጅራት ወደኋላ እንዲሉ ከሹፌሯ ውጭ ባለው ተጨማሪ ሰው መጫን የሚያስገድደውን ህግን ለሟሟላት አሻንጉሊቷን አለባብሱና አሳምራ ሰው አስመስላ ካሜራውን መሸወድ ብትችልም፤ ከተፈቀደው በላይ በፍጥነት በማሽከርከሯ ትራፊክ ሲይዛት መንገዱን ለመጠቀም የማትችል ሆና ተገኝታለች፡፡

የማይባል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ስለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ወደ ሌላኛው ጉዳያችን አመራን
የዳይኖሰር አጽም በጨረታ 44 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር አወጣ ቢባል ማን ያምናል፡፡ በኒውዮርክ ሶቴቢ በተሰኘ ጨረታ ግን ግዙፍ የዳይኖሰር አፅም በ44 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ በቅቷል፡፡

ቅጽል ስሙ አፔክስ የተሰኘው ዳይኖሰሩ 11 ጫማ (3.4 ሜትር) ቁመት እና 27 ጫማ ርዝመት ያለው ሲሆን የተሟላ አጽም ሆኖ መገኘቱ እስከ ዛሬ ከተገኙት አጽሞች የተሻለ ቁመናል እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡
የአፔክስ መገኛው እና የህይወት ቆይታው በአሜሪካ የነበረ ቢሆንም ጨረታው ያሸነፈ ሰው ግን ማንነቱ አልታወቀም፡፡ እንግዲ አፅሙ በጨረታ ምክንያት ከትውልድ ሀገሩ ይርቅ ይሆን ወይ? የሚለው ከባለቤቱ ድብቅ ማንነት ጋር የተደበቀ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ዳይኖሰሩ ከ150 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በጁራሲክ ዘመን የነበረ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ይህ ረዥም ዓመታት ያስቆጠረው የዳይኖሰር አፅም ነው እንግዲ 44 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ የቀረበው፡፡
የአፔክሰ አፅም በፈረንጆቹ 2022 በምዕራብ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት አቅራቢያ የተገኘ ነው፡፡በ2020 ቲራንኖሳዉረስ ሬክስ የተሰኘ የዳይኖሰር ቅሪተ አካል 31 ነጠብ 8 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠ ሲሆን የአፔክስ ሽያጭ 40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
አሁን ደግሞ ወደ ጃፓን አቀናን
በርካታ ተማሪዎች Ghost Pepper Chipsን ከተመገቡ በኋላ ወደ ሆስፒታል መግባታቸው ሌላኛው አስገራሚ ጉዳያችን ነው፡፡

በቶኪዮ ወደ 14 የሚደርሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች Ghost Pepper Chips ተጋርተው ከተመገቡ በኋላ ለሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ እና ለከፍተኛ የአፍ መቃጠል ተዳርገው ነው ሆስፒታል የገቡት፡፡
በዓለም እጅግ አቃጣይ የሆነውን ችብሱ በርካታ ቅመም እና የሚያቃጥል ቃሪያ የሚገኙበት ነው፡፡ኦዲቲ ሴንትራል እንደዘገበው ከተማሪዎች መካከል የተወሰኑት ችብሱን እንደተመገቡ ወዲያው በትምህርት ቤት ወድቀው ተገኝተዋል፡፡
ኢሶያማ ኮርፕ የተሰኘው የችብሱ አምራች ኩባንያው “18+ curry chips” የሚል ስያሜ የተሰጠው ችብስ “ከፍተኛ የደም ግፊት እና የጨጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች በጭራሽ መመገብ እንደሌለባቸው ያስጠነቅቃል፡፡
ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እዳይመገቡት ስለሚከለክል ተማሪዎቹ ህግ አለማክበራቸው ነው ለአደጋ ያጋለጣቸው እንደማለት ነው፡፡
የችብሱ የማቃጠል ደረጃ በቃላት የሚገለፅ አለመሆኑ ይነገርላታል እንግዲህ የቀበጡ ዕለት እንዲሉ ተማሪዎቹ እንደቀልድ ሞክረው ጉድ ሆነዋል፡፡












