፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሰጡት መግለጫ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 97 ነጥብ 5 በመቶው ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን እንዳልወሰዱ ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ጠዋት መጠናቀቁን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ፈተናው በመላ ሀገሪቱ በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 29ሺህ 718 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።የበይነ መረብ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠቱን ጠቅሰው፣ በቀጣይ ለሚሰጠው ፈተና የተሻለ ተሞክሮ የተገኘበት መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












