፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ከሐምሌ 3-11 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት መጠናቀቁን አስታውቋል።
ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት እንዲያገኙ የፈተና ቁሳቁሶችን አጅቦ የፈተና መስጫ ማዕከላት በማድረስ እና ለተፈታኝ ተማሪዎች ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ማድረጉንም የጋራ ግብር ኃይሉ ገልጿል።
ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ ሕብረተሰቡ እና የተማሪ ቤተሰቦች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም የፀጥታ አካላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት ስለተወጡም የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ምስጋና አቅርቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












