፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-የመገጭ የግድብ የስራ እንቅስቃሴን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ባዩህ አቡሀይ፣ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች እንዲሁም የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለፁት የጎንደር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት የሰራ አቅጣጫ መሰረት ለአዲስ ተቋራጭ ተሰጧል። ለአዲስ ኮንትራክተር ቅድሚያ ክፍያ ተሰጦት ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል ።
በፕሮጀክቱ በሁለት ዓመት በማጠናቀቅ የጎንደርን የንፅህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።መሰኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ጋር በመቀናጅት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የመገጭ ግድብ አማካሪ ማህንዲስ አቶ ወርቅነህ አሰፋ በበኩላቸው የግድቡ 57 ፐርሰንት ላይ ሲሆን በቀጣይ ሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












