፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 10 2016| NBC ETHIOPIA-ውልደቱ እ.ኤ.አ መጋቢት 19 1955 በምዕራብ ጀርመን ኢዳር-ኦበርስቴይን ነው። በሆሊውድ መንደር አሻራቸውን ማሳረፍ ከቻሉ የተዋጣላቸው ተዋናዮች መካከል ስሙ በቀዳሚነት ይነሳል። አሜሪካዊ ተዋናይ፣ ፕሮዲዩሰር እና ዘፋኝ ዋልተር ብሩስ ዊሊስ
የአሜሪካ ወታደር ከነበረው ዴቪድ ዊሊስ እና ከጀርመናዊ እናቱ ማርሊን የተወለደው ዋልተር ብሩስ እ.ኤ.አ በ1957 አባቱ ከውትድርና ከተሰናበተ በኃላ ቤተሰቡ ወደ ካርኒስ ፖይንት ኒው ጀርሲ ሊያቀና ችሏል።
ብሩስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካርኒስ ፖይንት ውስጥ በሚገኘው የፔንስ ግሮቭ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግብቶ ተከታትሏል።
በትምህርት ቤት ውስጥ ሲያወራ የምላስ መኮላተፍ ችግር የነበረበት ብሩስ በእድሜ እኩያ ተማሪዎች መሳለቅ ይደርስበት ነበር ። ለትወና ፍቅር የነበረው በመሆኑም በትምሀርት ቤት ውስጥ የሚገኝ የድራማ ክለብ በመቀላቀል በመድረክ ላይ በመጫወት በጊዜ ሂደት መንተባተቡን ሊቀንስ ችሏል። በትምህርት ቤት ቆይታውም ብሩስ የተማሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነ ለመረጥ ችሏል።

እ.ኤ.አ በ1973 ከፔንስ ግሮቭ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቆ መመረቅ ችሏል።ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተመረቀ በኋላ ዊሊስ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በጥበቃ ሰራተኝነት አገልግሏል።
በመቀጠልም በግል መርማሪነት ሲሰራ ቆይቶ ኃላ ላይ የተውና ዓለምን መቀላቀል ችሏል። እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ ሀ ብሎ የተቀላቀለው ትወና ከእውቅና ማማ ላይ አውጥቶታል፡፡
እ.ኤ.አ ከ1985 እስከ 1989 በተላለፈ Moonlighting አስቂኝ ተከታታይ ድራማ የመሪ ገጸ ባህሪን ወክሎ ለመጫወት ከሌሎች 3,000 ተዋናዮች ጋር ተወዳድሮ በማሸነፍ የዴቪድ አዲሰን ጁኒየር ገጸ ባህሪ መጫወት ቻለ።
በMoonlighting አስቂኝ ተከታታይ ድራማ እና ዘ ላስት ቦይ ስካውት ፊልም ዝናን መጎናጸፍ ቻለ።በአምስት ምዕራፎች የቀረበው ድራማው በምርጥ ተዋናይ ዘርፍ የኤሚ አዋርድ እና የጎልደን ግሎብ አዋርድ ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።
Die Hard (1988), Pulp Fiction (1994), The Fifth Element (1997), and the Sixth Sense (1999) ጨምሮ በርካታ የአክሽን ፊልሞች ላይ ተውኗል።
በ-ሀይማኖት ወርቁ












