፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 10 2016| NBC ETHIOPIA- ባላት በርካታ መስህብ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት UNESCO ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች በመላው አውሮፓ ከሚገኙ ተወዳጅ የቱሪስት መዳረሻዎችም አንዷ ናት ፡፡በደቡብ ምዕራብ አውሮፓ የምትገኘው ስፔን ፡፡
ስፔን ልዩ ልዩ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያላትና በርካታ የባህል ልዩነት ያላቸው ህዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት። በሞሮኮ የሜድትራኒያን የባሕር ዳርቻ ሰሜናዊ ጠረፍ የሚገኙ ቼውታና እና ሜሊላ በተባሉት መንደሮቿ ከአፍሪካ በመሬት የምትዋሰን ብቸኛዋ የአውሮፓ ሀገር ናት ፡፡
የስፔን ፀሐይና ወርቃማ የሆኑት የባሕር ዳርቻዎቿ እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ጥንታዊ የሥነ ጥበብና የምህንድስና ውጤቶች ዋና ዋናዎቹ የቱሪስት መስህቦቿ ናቸው።
ታሪካዊ ከተማ ፣ማራኪ የባህር ዳርቻዎች ፣ዘመን ተሸጋሪ ካቴደራሎች፣አስደናቂ ሙዚየሞቿ ፣ድልድዮች ፣ ሕንፃዎችና ሌሎች 47 ቅርሶች የዩኔስኮን ዓለም የቅርስ መስፈርቶችን በሟሟላት ያስመዘገበች የታደለች ሀገር ናት ስፔን፡፡
እነዚን ታሪካዊ ስፍራዎች ለመጎብኘት እና ለመዝናናት እ.ኤ.አ በ2022 ከ 100 ሚሊዮን በላይ አለማቀፍ ጎቢኚዎች ወደ ስፔን አቅንተዋል፡፡ሀገሪቱ ከዚ በተጨማሪም ከፍተኛ መጠን ያለው የወይን እና ወይራ ዘይት በማምረት በአለም ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የሚካሄዱ በርካታ ፌስቲቫሎቿ ደግሞ የበርካቶችን ቀልብ የሚገዙ ናቸው ፡፡ ከነዚህም ውስጥ የቡል ፌስቲቫል ተጠቃሽ ነው ፡፡ስፔን የቡል ፌስቲቫል ጀማሪ እንደሆነች ይነገራል ከሐምሌ 6 እስከ ሐምሌ 14 በየአመቱ የሚደረገውን የቡል ሩጫ ለመከታተል በርካታ ሰዎች ይጎርፋሉ ፡፡ ሌላኛው በአለም ላይ ትልቁ የምግብ ድብድብ ሊባል የሚችለው ላ ቶማቲና የተሰኘ በቲማንቲም የመወራወር ፌስቲቫልም ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ቱሪስቱን የምትስብበት ሃብቷ ነው፡፡
ማድሪድን ወደ ስፔን ያቀና ሁሉ ሳይጎበኛት አይመለስም ፡፡ ከ1561 ጀምሮ ዋና ከተማ ሆነ የምታገለግለው ማድሪድ የሀገሪቱ አብዛኛው ህብረተሰብ የሚኖርባት እና የዓለም አቀፍ ንግድ ማዕከልም በመባልም ትታወቃለች፡፡
ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ

በአንድ ወቅት የምዕራባውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ዋና መስጂድ እንደሆነ ይነገራል ፡፡ አሁን ላይ ላሜስኪታ በመባል የሚታወቀው የኮርዶባ ታላቁ መስጊድ ፡፡ ኮርዶባ በዓለም ላይ ካሉት ታላላቅ መስጂዶች አንዱ ሲሆን በስፔን የሕንፃ ግንባታ ጠበብቶች ከተገነቡት አስደናቂ ስራዎች አንዱ ነው ፡፡
ሴቪል ካቴድራል ወይም Cathedral of Saint Mary of the See በመባል የሚታወቀው ይህ ስፍራ በአለም ላይ ሶስተኛው ትልቁ ካቴደራል ነው ፡፡ የካቴደራሉ የኪነ ህንጻ ጥበብ እና የያዛቸው ታሪካዊ ቁሶች በበርካቶች ዘንድ ተመራጭ አድርጎታል፡፡
ኤል ሬስቶራንቴ ቦቲን

የስፔንን ምግብ ለማጣጣም ብለው የሚጓዙ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች አሉ። በብዛት ከሚገኙት ምግቦች መካከል የባሕር ምግቦች፣ በጭስ ወይም በጨው የደረቀ የአሳማ ሥጋ፣ እና ሌሎች ምግቦች ይጠቀሳሉ
የአለም ጥንታዊ ምግብ ቤት የት ነው አድራሻው ካሉም ስፔን ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1975 ስራውን የጀመረው El Restaurante Botín ምግብ ቤት በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ እውቅና የተሰጠው ጥንታዊው ምግብ ቤት ነው ፡፡
ሌላኛው ስፔን በአለም ላይ ዝናን እና እውቅናን ያተረፈችበት የእግር ኳስ ጨዋታ ነው ፡፡ የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝን ሁለት ለ አንድ ረታ ሻምፒዮን መሆኗን አረጋግጣለች፡፡
በ-የአብስራ ብርሃኑ












