፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 09 2016| NBC ETHIOPIA-የደቡብ ሜክሲኮ ግዛት በሆነችው ዋሃከ የዝናብ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የከፋ ድርቅ እያጋጠማት ይገኛል፡፡ ዋሃከ በተደጋጋሚ በድርቅ እየተጠቃች እንደሆነም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በግዛቲቷ የአየር ንብረት ለውጥ ትንበያ መሰረት በ2039 አመታዊ የዝናብ መጠኗ በ6 በመቶ ይቀንሳል፡፡
ግዛቲቷ በ2024 ከፍተኛ የሙቀት መጠን እያስተናገደች ነው፡፡ በግዛቷ የውሃ ጉድጓዶች ባዶ ሆነዋል፡፡ ዋሃከ ለህልውናዋ ስትልያጋጠማት የውሃ እጥረት በመዋጋት ላይ ትገኛለች፡፡
ድርቁ ለመኖር ስጋት የፈጠረባቸው የግዛቷ ነዋሪዎች ችግር ብልሀት ፈጥራል እንዲሉ ሁሉ ድርቅን ለመከላከል ብሎም ውሃን ለመጠበቅ ቅድመ አያቶቻቸው ይጠቀሙባቸው የነበረውን ጥንታዊ የውሃ መጠበቂያ መንገዶችን በድጋሜ ጥቅም ላይ እያዋሉ ይገኛሉ ሲል ቢ ቢ ሲ አስነብቧል፡፡
የውሃ እጦት ኑሯቸውን አደጋ ላይ የጣለው የግዛቷ ነዋሪዎች ከዘመኑ ወደ ኋላ ተጉዘው በቀደመው ጊዜ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲጠቀሙበት የነበረን የውሃን ደህንንነት እና ንጽናን ማስጠበቂያ ስልት ለመጠቀም ስለመገደዳቸው ይገልፃሉ፡፡
የ45 ዓመቷ አጉስቲና ኦርቲዝ ከ10 ዓመታት በላይ በአሜሪካ የነበራትን የስራ ቆይታ አጠናቃ ትውልድ መንደሯ ዋሃከ ስትመለስ የኑሮ ዜየዋ እንደቀደመው እንደማይሆን ጠንቅቃ ታውቅ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግራለች፡፡ በተለይም የአየር ንብረት ለውጡ ለኑሮዋ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ግምት እንደነበራት ጭምር፡፡
የውሃ እጥረቱን ለመከላከል በዚህ ዘመን እንደ ድሮ የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር መገደዷ እንደሚያስቆጫት ትገልፃለች፡፡

እ.ኤ.አ. በ2015 ዋሃከ በታሪኳ ከታዩት እጅግ የከፋውን ድርቅ ያስተናገደች ሲሆን 80 በመቶ የሚሆነው ግዛቱ ክፍል የውሃ ውጥረት አጋጥሞታል። የችግሩ አሳሳቢነት በአንድ አካባቢ የሆነ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር በተደጋጋሚ የሚከሰት ነው፡፡ ሜክሲኮም በአሁኑ ጊዜ ከአስር አመታት በላይ ታይቶ የማይታወቅ የተባለውን አስከፊ ድርቅ እየተዋጋች ነው፡፡
በግብርና ዘርፍ የተሰማራቸው፤ ኦርቲዝ ህይወቷን ለመቀየር ለምትለፋበት የግብርና ስራ እና ለዕለት ተዕለት ኑሮ የምትጠቀምበት የውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ችግሩ እጅግ ያሳስባት እንደነበር ገልጻለች፡፡
የሜክሲኮ ብሄራዊ የውሃ ኮሚሽን በአካባቢው የሚኖረው የውሃ አቅርቦት አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ ድርቅ ሊያጋጥም እንደሚችል በተደጋጋሚ ጠቁሟል፡፡ የዝናብ እጥረቱም በግብርና ምርት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሲያሳደር ሰንብቷል፡፡ የሀገሪቷ መንግስት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የዋሃከ አከባቢ የሚያገኘው አመታዊ የዝናብ መጠን በአማካይ 1,550mm (61in) ነው። ይህም እንደ ኦርቲዝ ላሉ ማህበረሰቦች ሰብል ለማልማት፣ ምግብ ለማግኘት እና እንስሳቸውን ለማራባት በቂ አይደለም፡፡ በዚህም የተነሳ ህጻናቱ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እያጋጠማቸው ይገኛል፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ በዙሪያቸው የሚገኙ ጥቂት የውሃ ምንጮችን እንዳይጠቀሙ አብዛኞቹ የተበከሉ ናቸው፡፡
ኦርቲዝ ዕለት ተዕለት ኑሯን ለመግፋት በግብርናው ዘርፍ ሰብሎችን እንዳታመርት የውሃ እጥረቱ ማነቆ ሆነባት በዚህም ወደ ጓሮ አትክልት ፊቷን በማዞር እ.ኤ.አ. በ2019 ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ባቄላ ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት እና ሌሎች የሀገር በቀል ምርቶችን ማምረት ተያያዙት፡፡ በስራቸው ስኬታማ ቢሆኑም ፕሮጀክቱ ለአየር ንብረት ተጽእኖ የተጋለጠ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁ ኖሯል፡፡
የሰጉትም አልቀረም ስኬታማ ወራት በኋላ ምርታቸው በድርቅ ሊጓዳ ችሏል፡፡ ከ30 ዓመታት በፊት በሜክሲኮ ከተማ የተመሰረተው ትምህርት እና ዘላቂ ልማትን ከሚያስተዋውቀው ከግሩፔድሳክ (Grupedsac) ድርጅት ጋር አብረው መስራት ጀመሩ።
ድርጅቱ ችግሩን ለመቅረፍ ቀደምት አያቶች ውሃን እና መሬታቸውን እንዴት ያስተዳድሩ እንደነበር ለአካባቢው ነዋሪዎች ማስገንዘብ ጀመረ፡፡ ግሩፔድሳክ ከኦርቲዝ ማህበረሰብ ጋር መስራት ሲጀምር የድርቅ ስጋቱ በመጨመሩ ሰብሎችን ማልማት እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡
ኦርቲዝ ከድርጅቱ ጋር በመጣመር 20,000 ሊትር (5,283 ጋሎን) የመያዝ አቅም ያለው ከሲሚንቶ የተሠራ የውሃ ማጠራቀሚያ በአካባቢው በሚገኘው ትምህርት ቤት በመገንባት ችግራቸውን የሚቀርፉበትን የተስፋ መንገድ አሃዱ አሉ፡፡ በውኃ ጉድጓዱ የዝናብ ውሃን በማጠራቀም ለጽዳት, ለምግብ ማብሰያ እና ለመስኖ መጠቀም ጀመሩ፡፡ የውሃ ማጠራቀሚያው በባክቴሪያን፣ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን እና ሌሎች ጎጂ ንጥረ ነገሮችን እንዳይበከል ውሃውን የሚያጸዳ አብሮ የተሰራ ማጣሪያ ተበጅቶለታል፡፡ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተገንብቶ የነበረው የውሃ ጉድጓድ አሁን በዋሃከ ግዛት በእያንዳንዱ መኖሪያ ቤት በመገንባት ስር የሰደደውን ችግር ለመቅረፍ ተችሏል፡፡ የተበከለ ውሃን እንዴት ማከም እንደሚችሉ ማወቃቸው በእጅጉ እንደረዳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ያነሳሉ፡፡ አሁን ኦርቲዝ የሰብል ምርችን በድጋሚ ማምረት ጀምራለች፡፡
አሁን የዋሃከ ነዋሪዎች የቀደመውን ዘዴ በመጠቀም ለጊዜውም ቢሆን የውሃ እጥርት ችግሩን ማስታገስ ችለዋል፡፡ ነገር ግን ዘላቂ መፍትሄ መሆን የሚችለው የአየር ንብረትን መጠበቅ እንደሆነ የማይካድ ሃቅ ነው እና ለአየር ንብረት ለውጡ ለመከላከል የሁሉንም ርብርብ የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡











