፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 06 2016| NBC ETHIOPIA- የአገር መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታንና በክሊኒካል ነርሲንግ ሞያ በዲፕሎማ ያስተማራቸውን 800 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
በምርቃ መርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ተገኝተዋል።


ተማራቂዎቹ በድሬደዋ በሚገኘው የምስራቅ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታል ትምህርታቸውን ለሁለት ዓመታት ከስድስት ወራት በንድፍ ሀሳብ እና በተግባር የተከታተሉና በደረጃ አራት በዲፕሎማ መመረቃቸውን ተገልጿል።

ምስራቅ ዕዝ የደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ኃላፊ ኮሎኔል ብርሃኑ ዘውዱ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ተመራቂዎቹ ከሁሉም የመከላከያ ዕዝ የተመለመሉ የሠራዊት አባላት ናቸው።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












