፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA-የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎም ይጠበቃል።
ጉባኤው በዛሬው ውሎ የምክር ቤቱን የ2016 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2017 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አድምጦ እንደሚያጸድቅ ተገልጿል።
በተጨማሪም የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።
የወጣው መርሀ-ግብር እንደሚያሳየው የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድና የማስፈጸሚያ በጀትም ቀርቦ በጉባኤው ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል።
በጉባኤው የተለያዩ አዋጆችም ቀርበው የሚጸድቁ ሲሆን የዳኛ ሽኝትና ሹመትም እንደሚኖር ተመላክቷል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












