፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ እንደሚገኝ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን ተክለናል ብለዋል። የህብረተሰባችንም የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።


በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑ ነው ሲሉም አክለዋል።
ከሀረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ህዝቦቻችን አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረውን ክህሎታቸውን አካፍለውናል ብለዋል።


በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












