፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 03 2016| NBC ETHIOPIA- ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢው 93 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማግኘት መቻሉን አስታወቀ። ገቢው ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ21 ነጥብ 7 በመቶ ወይም የ16 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ የተገኘበት መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ደንበኞች በ2015 በጀት ዓመት 72 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ደንበኞቹ 78 ነጥብ 3 ሚሊየን መድረሳቸውን ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል። ኩባንያው በበጀት ዓመቱ 198 ነጥብ 02 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስገባት ችሏል።
የፋይናንስ ተደራሽነት እና አካታችነትን በመጨመር በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር በቴሌብር የተከናወነ ሲሆን ቴሌ ብር አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 2 ነጥብ 55 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር ተፈፅሟል።
በተጠናቀው የ2016 በጀት ዓመት ኩበንያው ካስቀመጠው የሦስት አመት የእድገት ስትራቴጂ ሁለተኛው ዓመት ነው።የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት ዓመቱ የደንበኞችን ፍላጎት ለሟሟላት እና የአኗኗር ዘዬን ለማዘመን በተደረገው ጥረት 251 የቴክሎጂ መተግበሪያዎች ለማስተዎወቅ ታቅዶ 270 መተግበሪያዎች ለደንበኞች ማቅረብ መቻሉን ተገልጿል። ከዚህም መካከል 127 ያህሉ አዳዲስ መተግበሪያዎች ናቸው ብለዋል።

በበጀት አመቱ በገጠር አከባቢዎች 462 አዳዲሰ ተጨማሪ የሞባይል ኔትወርክ ሳይቶች መዘረጋቱን የገለጹት የአትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ይህም 7 ሚሊየን ተጨማሪ የሞባይል ኔትወርክ አቅም ለመፍጠር መቻሉን አስታውቀዋል።
1ሺ167 ታወሮች በፋይበር መገናኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለም ሀገራት ጋር የኦፕቲካል ፋይበርን በመጠቀም በምትገናኝባቸው በኬኒያ፣ ሶማሌላንድ፣ ሱዳን እና በጅቡቲ ሁለት መውጫዎችን በመጠቀም ስታከናውን የነበረው ዓለማቀፋዊ ግንኙነት በ21 መቶ ማደጉ ተመላክቷል።
በበጀት ዓመቱ በ5 የተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ 570 ኪ.ሜ የሚጠጉ የባክቦን ፋይበር መስመሮችን መጠገን መቻሉ ተገልጿል።ኢትዮ ቴሌኮም 1ሚሊዮን የዲጃታል መታወቂያ ለመመዝገብ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የገለፁ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከታቀደው በላይ የተሰራበት ነው ብለዋል።

የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የሀይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ የኦፕቲካል ፋይበር መስመሮች እና የአገልግሎት እቃዎች መሰረቅ፣ የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ቦታ አለማግኘት እንዲሁም የፀጥታ ችግር ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ያጋጠመው ፈተናዎች እንደነበሩ ተነስቷል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












