፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 27 2016| NBC ETHIOPIA-የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ::
ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለፈተና ቁሳቁሶች እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባዘጋጀው የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መልዕክት በመላክ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል ጥቆማ እንዲሰጥ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን አቅርቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












