Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የዓለማችን ምርጥ ቴያትር ቤቶች

July 3, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 26 2016| NBC ETHIOPIA-የሰው ልጅ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ባህል፣ አኗኗር እና ማንነት ዘመናትን ተሻግሮ ለአዲሱ ትውልድ ያወሳ ዘንድ ቲያትር በሰው ልጅ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ አንዳንድ ቲያትር ቤቶች ከኪነ-ህንጻቸው ውበት ባሻገር በታሪካዊ ፋይዳቸውና ለጥበቡ ዓለም ባበረከቱት አስተዋጽዖ ስማቸው ጎልቶ ይጠራል፡፡

ቴክኖሎጂ፣ ቢዝነስና መዝናኛን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ጥናቶችን የሚያደርገውና በአሜሪካ መቀመጫውን ያደረገው ዎክ ዌቭስ መጽሄት በኪነ-ህንጻ ጥበባቸው እና እድሜ ጠገብነትን ከዘመናዊት ጋር ያጣመሩ ያላቸውን ቲያትር ቤቶች ምርጥ አምስቱን እንነግራችሁ፡፡ 

በዩናይትድ ኪንግደም መዲና ለንደን መገኛውን ያደረገው ዘ ሮያል ኦፔራ ሃውስ የዩናይትድ ኪንግደም የኪነ-ጥበብ ዘርፍ መለያ ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ስር መሰረቱ ወደ 18ኛው ክፍለ ዘመን የሚወስደን ቲያትር ቤቱ ከጎርጎሮሳውያኑ 1732 ጀምሮ የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ይሰሩበት ነበር፡፡

በዩናይትድ ኪንግደም መዲና ለንደን መገኛውን ያደረገው ዘ ሮያል ኦፔራ ሃውስ የዩናይትድ ኪንግደም የኪነ-ጥበብ ዘርፍ መለያ ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ስር መሰረቱ ወደ 18ኛው ክፍለ ዘመን የሚወስደን ቲያትር ቤቱ ከጎርጎሮሳውያኑ 1732 ጀምሮ የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ይሰሩበት ነበር፡፡

የሮያል ኦፔራ ሃውስ ዓለም ዓቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ታላላቅ ኦፔራዎችን፣ አስደሳች የባሌ ዳንሶች እና ታላላቅ ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት እውቅናን አትርፏል፡፡ የኪነጥበብን ተደራሽነት ለማስፋት ደፋ ቀና የሚለው ማዕከሉ የጥበብ አፍቃሪያንን ወዳለበት መምጣት የግድ ሳይል በተለያዩ ዘመን አመጣሽ አማራጮች የልፋቱን ፍሬ በመላው ዓለም ለሚገኙ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የጥበብ አፍቃሪያን ያደርሳል፡፡

ባለዝናው ዘ ሮያል ኦፔራ ሃውስ አሁን ያለውን ታሪካዊነትን ከዘመናዊነት ያጣመረ ይዞታ የያዘው በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1990ዎቹ መጨረሻ ላይ በተደረገለት እድሳት አማካኝነት ነው፡፡ በቀይ ቀለም ያጌጠ ሰፊ አዳራሽ እና የሚያብረቀርቅ የወርቅ ጌጥ ለ”ዘ ሮያል ኦፔራ ሃውስ” ወደር የለሽ ታላቅ ድባብን ፈጥረውለታል፡፡

በመላው ዓለም ዛሬም ድረስ ተወዳጅነታቸውን ይዘው መቀጠል የቻሉ፣ እንደ ቅርስ የሚሳሳላቸው ሙዚቃዎች ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በጎርጎሮሳውያኑ 1778 የተመሰረተው እና በጣሊያኗ ሚላን እምብርት መገኛውን ያደረገው “ላ ስካላ” በሌላኛው መጠሪያ “ቲአትሮ አላ ስካላ”፡፡

ድንቅ የኪነ-ህንጻ ስራው አድናቆትን ያጎረፈለት “ላ ስካላ” ፈረስ የሚያስጋልብ ይዞታ ባለቤት ነው፡፡ ኦፔራ እና መገኛው ጣሊያን መሆኑ የሚነገርለትን የባሌ ዳንስ ትርኢት ማየትስ “ላ ስካላ” ነው እስኪባልለት ድረስ የባሌ ዳንስ ትርኢቶች፣ በሙዚቃው ዓለም ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፉ የኦፔራ እና የክላሲካል ሙዚቃ ዝግጅቶች ተሰናድተውበታል፡፡ ቲያትር ቤቱ ታሪካዊነቱን ሳይለቅ ሳይለቅ ዘመኑን መስሎ ይጓጓ ዘንድ ተደጋጋሚ እድሳቶች ተደርገውለታል፡፡

የታላቅ ህንጻ ባለቤቱ የቦልሾይ ቲያትር የሩሲያ ባህል እና ጥበብ መገኛ ጥንታዊ ማዕከል ነው፡፡ በሩሲያ መዲና ሞስኮ መገኛውን ያደረገው ቲያትር ቤቱ ጅማሮው በጎርጎሮሳውያ 1824 መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ሰፊው የመሰብሰቢያ አዳራሹ ግድግዳዎቹ በሳቢ ቀለማትና በወርቅ ጌጣ ጌጦች፣ ጣሪያው ደግሞ ትኩረትን በሚጠይቁ ውስብስብ ምስሎች ያሸበረቀ ነው፡፡

በጎርጎሮሳውያኑ 2011 የተጠናቀቀው እድሳቱ ዘመናዊ የመድረክ ቴክኖሎጂን ከታሪካዊ ውበት ጋር በማጣመር ለተመልካቾቹ ጥራታቸውን የጠበቁ ማራኪ የጥበብ ስራዎች እንዲያደርስ አግዞታል፡፡ ጥንታዊነቱን ያለቀቀው ይዞታው የብዙዎችን ዕይታ ይስባል፡፡

የሩሲያ የጥበብ ዘርፍ እድገት ያመጣ ዘንድ የቦልሾይ ቲያትር ቤት ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል፡፡ ይህም የሩሲያ ባህል የማዕዘን ድንጋይ ነው በሚል የተሰጠውን ሙገሳ እንደያዘ ዘመንን እንዲሻገር አስችሎታል፡፡ 

በሩሲያ ምድር ጥራቱን የጠበቀና አስደሳች የባሌ ዳንስ ትርኢት እና ኦፔራ ማግኘት የፈለገ የጥበብ አፍቃሪ እግሮች ያዘወትሩበታል፡፡ የቻይኮቭስኪን ስዋን ሌክ እና እና የፕሮኮፊየቭን “ሮሚዮና ጁሊየት”ን ጨምሮ ዘመን የማይሽራቸው የጥበብ ስራዎች በማቅረብ ከመላው ዓለም የጥበብ አፍቃሪያንን እየሳበ ይገኛል፡፡

የድንቅ ስነ-ህንፃ እና የዘመናዊነት ምልክት “ሲድኒ ኦፔራ ሃውስ” አውስትራሊያ የምትኮራበት ዝነኛ ሕንፃ ሆኖ ስሟን በማስጠራቱ ብቻ አይደለም፣ በዓለም ካሉ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ማሳያ ስፍራዎች አንዱ በመሆን ጭምር እንጂ፡፡

በጎርጎሮሳውያኑ 1973 አገልግሎት መስጠት የጀመረው በአውስትራሊያዋ ሲድኒ መገኛውን ያደረገው “ሲድኒ ኦፔራ ሃውስ” ለየት ያለው የኪነ-ህንጻ ንድፉ ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ውበትን ከውጫዊ ውበት ጋር አጣምሮ የያዘ ስለመሆኑ ብዙዎች መስክረውለታል፡፡

ኪነ-ህንፃ እና ጥበብ ሲጣመሩ በህብረተሰብ እና ባህል ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ ማሳያ ነው ተብሎ ይሞካሻል፡፡ ለባህላዊ ጥበባት ማዕከል የሆነው የሲድኒ ኦፔራ ሃውስ በውስጡ ለኮንሰርትና ትላልቅ ዝግጅቶች የሚሆኑ ሰፋፊ አዳራሾችን ይዟል፡፡ የዓለም ስመጥር የጥበብ ሰዎች ለስራዎቻቸው ምቹ መድረክ ሲሉ ይመርጡታል፡፡

ኦፔራ፣ ቲያትር፣ ሙዚቃ እና ዳንስን ጨምሮ በየዓመቱ ከ1 ሺህ 500 በላይ ትርኢቶችን ያስተናግዳል፡፡ ታዲያ እነኚህን ዝግጅቶቹን ለመመልከት በዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች ወደ እዚህ ማዕከል እንደሚተሙ ይነገራል፡፡ ታዲያ ለእነኚህ መሰናዶዎቹ የሚመጥን ይዞታ ይኖረው ዘንድ በተለያዩ ጊዜያት ጥገናና ማሻሻያዎች ተደርገውለታል፡፡

የመጨረሻው የቲያትር ቤት መዳረሻችን ወደ ቼክ ሪፐብሊክ ይወስደናል፡፡ በመዲናዋ ፕራግ የሚገኘው “ብሄራዊ ቲያትር” የሃገሪቱ ብሄራዊ ማንነት እና ኩራት ወኪል ሆኖ ይታያል፡፡ ውጫዊ ውበትን ከውስጣዊ ውበት አጣምሮ የያዘው ቲያትር ቤቱ ከፊት ለፊቱ የሚፈሰው የቭልታቫ ወንዝ ከፕራግ ዝነኛ ምልክቶች አንዱ አድርጎታል፡፡

በ19ኛውና በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ መካከል በነበረው የሥነ-ሕንፃ ዘመን የተገነቡ ህንጻዎች “Neo-Renaissance building” የሚል መጠሪያ ነበራቸው፡፡ ይህን መጠሪያ ከያዙት መካከል የሆነውና በጎርጎሮሳውያኑ 1881 የተከፈተው ቲያትር ቤቱ የግንባታ ወጪው በሀገሪቱ ህዝብ የገንዘብ መዋጮ የተሸፈነ ነው፡፡

ውስጠኛ ክፍሉ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርስነቱን በሚያሳብቁ ግብዓቶች የተሞላ ነው፡፡ ኦፔራ፣ የባሌ ዳንስ ትርኢቶች እና ድራማዎችን ጨምሮ የቼክ ስር የሰደደ ባሕል የሚንጸባረቅባቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርቡበታል፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

ከ1 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ተደራሽ የሚሆኑበት የክትባት ዘመቻ ተጀመረ

Next Post

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል መግለጫ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል መግለጫ

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል መግለጫ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ስለዋጋ ግሽበት የሰጡት ምላሽ  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ስለዋጋ ግሽበት የሰጡት ምላሽ  

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?