፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 25 2016| NBC ETHIOPIA- ከ1 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ተደራሽ የሚሆኑበት ሀገር አቀፍ የክትባት ዘመቻ በዛሬው ዕለት መጀመሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሀገር አቀፍ የክትባት ዘመቻውን አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ለመገናኛ ብዙኀን መግለጫ ተሰጥተዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት በሚቆየው የማካካሻ እና የተደራሽነት የክትባት ዘመቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት።
ክትባቱ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ክትባት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ህጻናትን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑ ዶ/ር ደረጀ አብራርተዋል።
የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።በዚህ የክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ተጠቃሚ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን፤ ወላጆችና አሳዳጊዎች ህጻናቶቹን በማስከተብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












