፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 25 2016| NBC ETHIOPIA-ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ ሰላም መረጋገጥ ሊኖራቸው በሚገባ ሚና ዙሪያ የሚመክር ሃገር አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
“ሚዲያዎቻችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው መርሃ ግብር የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በትብብር ያዘጋጀው ነው።
በመድረኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠንከር የሚዲያ ሚና የጎላ መሆኑን ያነሱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሃመድ እድሪስ መድረኩ ሚዲያዎች በሰላም ግንባታ ረገድ ስላለባቸው ሃላፊነት የሚያሳስብ እንደሆነ ገልፀዋል።
የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው መድረኩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ግንባታ ሂደት ሚዲያ ያለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ በመፈተሽ በጎውን ለማስቀጠል ብሎም ስህተቱን ለማረም ያለመ ነው ብለዋል።
ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የሚዲያ ሀላፊዎች እና የቋማት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዎች ተሳትፈውበታል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












