Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የመጀመሪያው የሚጥል በሽታን የሚቆጣጠር መሳሪያ

June 27, 2024
in Health, News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 20 2016| NBC ETHIOPIA- የሚጥል በሽታ በነርቭ መታወክ የተነሳ ተደጋጋሚ የሆነ በሰዉነት ላይ ማንቀጥቀጥን፣ የጡንቻ መገታተርን እና ማርገፍገፍን የሚያስከትል በሽታ ነዉ።በሽታው በማንኛዉም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሰት ሲሆን በአብዛኛዉ በልጆች እና አዛዉንቶች ላይ ይታያል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ 50 ሚሊየን ሰዎች የሚጥል በሽታ እንዳለባቸው ይገልፃል፤ ድርጅቱ በአመቱ ቢያንስ 5 ሚሊየን ሰዎች ለሚጥል በሽታ ይዳረጋሉ ይላል፡፡

ቢቢሲ በጤና አምዱ ላይ ባወጣው መረጃ በዓለም የመጀመሪያው የሚጥል በሽታ መቆጣጠሪያ መሳሪያ በአንድ ታዳጊ ወንድ ልጅ ጭንቅላት ውስጥ ተገጥሟል ይላል፡፡

በከባድ የሚጥል በሽታ ለአመታት ሲሰቃይ የነበረው ታዳጊው ኦራን ኖውልሰን በራስ ቅሉ ውስጥ ህመሙን ለመቆጣጠር ያስችላል ተባለ መሳሪያ የተገጠመለት የመጀመሪያው ታካሚ ሆኗል፡፡

ኦራን ኖውልሰን ሌኖክስ-ጋስታውት ሲንድረም በተባለ የሚጥል በሽጣ ከሶስት አመቱ ጀምሮ ሲሰቃይ እንደነበር ወላጅ እናቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ትገልፃለች፡፡

በጥቅምት ለንደን በሚገኘው ግሬት ኦርመንድ ስትሪት ሆስፒታል ኦራን የ12 አመት ታዳጊ ሳለ ቀዶ ጥገናው የተካሄደ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ እናቱ አንስታለች፡፡ ኦራን አሁን 13 ዓመት ታዳጊ ሆኗል፡፡ጤንነቱም ላይ ለውጥ እንዳለ እናቱ ጀስቲን ትገልጻለች፡፡

በአንጎል ውስጥ የተገጠመለት እንደ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ የሚያገለግለው ኒውሮስቲሙላተር የኤሌክትሪክ ምልክቶችን ወደ አንጎል ወይም ወደ ነርቭ ሥርዓትን የሚያደርስ ክፍል ነው፡፡ ህመምን ለመግታት ወይም የነርቭ በሽታዎችን ለማከም ኒውሮስቲሙላተር  ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡

ኦራን የመቆጣጠሪያ መሳሪያው በጭንቅላቱ ቅል ውስጥ ከተቀበረ በኋላ  የኤሌክትሪክ ምልክቶችን ወደ አንጎል እና ሌሎች አካል ክፍሎች የሚልከው ኒውሮስቲሙላተር ታዳጊው ያለበትን የሚጥል በሽታ 80% ቀንሷል ይላል ቢቢሲ ያወጣው መረጃ።

ትውልደ እንግሊዚያዊው ኦራን መቆጣጠሪያ መሳሪያው ከተገጠመለት በኋላ ከፍተኛ ለውጦችን ማሳየት መቻሉ መሳሪያው ተስፋ ሰጪ እንደሆነ የሚያመላክት ነው እየተባለ ይገኛል፡፡

የኦራን እናት ጀስቲን መሳሪያው ከተቀበረ በኋላ ልጇ የበለጠ ደስተኛ መሆኑን እና በበሽታው ምክንያት ይወድቅ የነበረበት ጊዜ መቀነሱን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

በጥቅምት ለንደን በሚገኘው ግሬት ኦርመንድ ስትሪት ሆስፒታል ኦራን የ12 አመት ታዳጊ ሳለ ቀዶ ጥገናው የተካሄደ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ እናቱ አንስታለች፡፡

የሌኖክስ-ጋስታውት ሲንድሮም የሚጥል በሽታ ከ100 ሕፃናት ውስጥ 1 ወይም 2 ያህል እንደሚከሰት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ህመሙ  ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚገኙ ልጆች ላይ በተደጋጋሚ የሚያጋጥም ነው፡፡  ሆኖም አልፎ አልፎ እስከ 18 ወራት ባለው ጊዜ እና እስከ 10 አመት እድሜ ድረስ ህመሙ ሊከሰት ይችላል፡፡

ለአመታት የልጅነት ጊዜውን ህመሙ ነጥቆታል የምትለው እናቱ ልጇን ላለማጣት ትንፋሹ እንደሚቋረጥ እና ችግሩ የከፋ እንዳይሆን የተለያዩ መድሀኒቶች በመስጠት ጊዜዋን ስታሳልፍ እንደነበር በማስታወስ የህመሙን አስከፊነት ትገልጻለች፡፡

በጣም ፈጣን የሶስት አመት ልጅ ነበረኝ የምትለው ጀሲቲን መታመም በጀመረ በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ክህሎቶቹን ማጣቱን ትናገራለች፡፡ ኦራን ኦቲዝምን ጨምሮ ትኩረት ማጣት ችግር ያለበት ሲሆን የሚጥለው በሽታ ግን ከሁሉም የከፋው እንደሆነ መናገሯን ቢቢሲ በጤና አምዱ አስፍሯል፡፡ ለኦራን የተገጠመው መሳሪያ አንጎሉ ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ለማስተካከል የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

ጀስቲን ልጇን በሙሉ ጤንነት ለማግኘት እንደምትፈልግ እና የልጇ የአመታት ስቃይ እንዲያበቃ ምኞቷ እንደሆነ ስምንት ሰአታት ከፈጀው ቀዶ ጥገና በፊት ለቢቢሲ ተናግራለች፡፡የሕፃናት የነርቭ ቀዶ ጥገና ዶክተር ማርቲን ቲስዳል እና ቡድኑ በኦራን የጭንቅላት ቅል ውስጥ  የገጠሙት አዲሱን መሳሪያ 3.5 ሴንቲ ሜትር ስኩዌር እና 0.6 ሴንቲ ሜትር ውፍረት ያለው መሆኑን እና በራስ ቅሉ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።ጫፎቹም ከኒውሮስቲሙሌተር ጋር የተገናኙ ሲሆን በህክምና ሂደቱ ውስጥ ሊከስት የሚችለው የስህተት አጋጣሚ ከአንድ ሚሊሜትር ያነሰ እንደነበር ዶክተር ማርቲን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ጥልቅ የአንጎል ማነቃቂያ መሳሪያ የሚጥል በሽታ ላለባቸው ልጆች ተሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኒውሮስቲሚተሮች በደረት ውስጥ ተቀምጠው ሽቦዎች ወደ አንጎል እንዲዘረጉ ያደርጉ እንደነበር የቀዶ ጥገባ ባለሙያው አስታውሰዋል፡፡ ይህም የህጻናቱን ስቃይ የሚያበረታ ነበር ብለዋል፡፡ አዲስ የተገጠመው መሳሪያ ግን ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ ውስብስብ ችግሮች እና የኢንፌክሽን አደጋን እንደሚቀንስ ተስፋ እናደርጋለን ምክንያቱም የሚተከለው የራስ ቅሉ ውስጥ እንጂ በደረት ውስጥ አይደለም” ብለዋል ዶክተር ማርቲን፡፡

የመሣሪያውን ባትሪውን በየቀኑ በገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎቹ ቻርጅ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ኦራን ወደ ቀድሞው ህይወቱ መመለሱ ተገልጿል፡፡

ኦራን እና ቤተሰቡን ቢቢሲ ከሰባት ወር በኋላ ለመመልከት ወደ መኖሪያ ቤታቸው ያቀና ሲሆን በኦራን ህይወት ውስጥ ትልቅ መሻሻል እንዳለ እና እጅግ ንቁ እንደሆነ እናቱ ጀሲትን ገልጻለች፡፡ ይህም አዲስ የህክምና ዜዴ በሚጥል በሽታ ለአመታት ለሚሰቃዩ ህጻናት እጅግ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ታምኗል፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

የኢትዮጵያ ልዑክ 47ኛውን የጂቡቲ የነጻነት ቀን ለመታደም ጅቡቲ ገባ

Next Post

በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ምን ውጤቶችን አስመዘገቡ?

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ምን ውጤቶችን አስመዘገቡ?

በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ምን ውጤቶችን አስመዘገቡ?

ተሽከርካሪ የሰረቀችው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበች

ተሽከርካሪ የሰረቀችው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበች

የአሜሪካን ጎት ታለንት “Golden buzzer” አሸናፊዎች

የአሜሪካን ጎት ታለንት “Golden buzzer” አሸናፊዎች

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?