፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 19 2016| NBC ETHIOPIA-በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ ከግለሰቦች ሞባይል በመንጠቅ ሱቅ ውስጥ ሲያከመቹ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ።
አቶ ሱራፌል ቢያብል በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፀሚ ሲሆኑ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት 2 ተጠርጣሪዎች በጥቁር ሞተር ሳይክል ኮድ 2,A 19,21,6 ደ.ሕ( ደቡብ ህዝብ) መልኩ ጥቁር በሆነ 1ኛ ተጠርጣሪ እያሽከረከረ ፣ 2ኛ ተጠርጣሪ ሞተር ሳይክል ላይ ከኋላ በመሆን ከግለሰቡ ነጥቀው በፍጥነት እያሽከረከሩ ከአካባቢው ይሰወራሉ።

የግል ተበዳይ ወንጀሉ እንደተፈፀመባቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለገርጂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ያመለክታሉ ። ፖሊስም የግል ተበዳዩን አቤቱታ በመቀበል ባደረገው ክትትል ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ከሌቦቹ የሚረከቡ 2 ተጠርጣሪዎች በድምሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ህግን በተከተለ አግባብ ባደረገው ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ተከራይተው የሞባይል ጥገና የሚሰሩበት ሱቅ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ግለሰቦች ተቀምተው የተከማቹ 32 ስማርት ሞባይል ስልኮችን በኤግዚቢት ተይዘዋል ።

የንግድ ሱቆችን በመከራየት ወንጀል የሚፈፅሙ እና የሚያስፈፅሙ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል ።
ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል የሚል ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መውሰድ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












