Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት አዋጅ ፀደቀ

June 25, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 18 2016| NBC ETHIOPIA-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ /ማሻሻያ/ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል።

ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ በምክር ቤቱ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ገዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

በተሻሻለው አዋጅ በፌዴራል ደረጃ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች የካሳ ትመና ክፍያ እንዲሁም ተነሺዎችን መልሶ ለማቋቋም ስልጣንና ኃላፊነት ያለባቸውን አካላት በግልፅ ለይቶ ለመወሰን የሚያስችል ስርአት ስለመዘርጋቱ ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቶች በጥራት እና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲከናወኑና ለሀገራዊ ልማት ያላቸውን አስተዋጽዖ ከፍ የሚያደርግ ድንጋጌ በአዋጁ ስለመካታቱም አስረድተዋል። ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ ወጪና ተቀራራቢ ጊዜ እንዲጠናቀቁ የሚያስችል አሰራር ያስቀመጠ አዋጅ እንደሆነም ተናግረዋል።

ተገቢ ባልሆነ የካሳ ይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱት የፍርድ ቤት ክርክርና የባንክ አካውንት እገዳ በፕሮጀክቶች ላይ ይደርስ የነበረውን የስራ መጓተት የሚቀንስ አዋጅ እንደሆነም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተገልጿል።

በምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው ቀደም ሲል የነበረው የካሳ ክፍያ ስርዓት ለብልሹ አሰራሮች የተጋለጠ መሆኑንና የልማት ተነሺዎች ተገቢውን ካሳ እንደማያገኙ ጠቁመው፤ የተሻሻለው አዋጅ የመንግስት እና የህዝብ ሀብት እንዳይባክን ያስችላል ብለዋል፡፡

አዲሱ አዋጅ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚያመጣው ችግር እንደሌለና ተገቢ ካሳ ያላገኘ አካል እስከ ላይኛው የፍትህ ተቋም በመሄድ መብቱን ማስከበር እንደሚችልም የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የተሻሻለው አዋጅ ቀደም ሲል የነበረውን ብልሹ አሰራር በመቅረፍ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው በጀትና ጊዜ እንዲጠናቀቁ ያግዛል ብለዋል፡፡

ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚነሱ አለመግባባቶች ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሚመጡ እዚያው ባሉበት ፍርድ ቤቶች ቢታዩ የሚሉ አስተያየቶችም ተነስተዋል፡፡

በሌላ በኩል አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የካሳ ክፍያ ለማከናወን አቅም ላይኖራቸው እንደሚችል ለቀረበው ጥያቄ፤ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ለክልሎች የሚመደበው በጀት ላይ የካሳ ክፍያን ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በተሻሻለው አዋጅ የተፈጻሚነት ወሰን አዋጁ ከጸደቀ በኋላ ለሚሰሩት የካሳ ግመታዎችና ክፍያዎች ሲሆን፤ ቀደም ሲል የካሳ ግመታ ተሰርቶ ያልተከፈላቸው የልማት ተነሺዎች ግን በነባሩ አዋጅ እንደሚስተናገዱ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም ረቂቅ አዋጁ በ 4 ተቃውሞ እና በ 6 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 ሆኖ ጸድቋል፡፡

????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

????Website – https://nbcethiopia.com/news/

????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

35ተኛው የአፍሪካ ኒኩልየር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር ልማት(AFRA) ጉባኤ መክፍቻ

Next Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

የአለማችን ረጅሙ ውሻ

የአለማችን ረጅሙ ውሻ

የካዛኪስታኑ አወዛጋቢ ፊልም—ቦራት

የካዛኪስታኑ አወዛጋቢ ፊልም---ቦራት

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?