፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 14 2016| NBC ETHIOPIA- በዘመናት የጊዜ ሂደት በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በመታገዝ እጅን በአፍ የሚያሲዙ እና ሃሳብን የሚሰርቁ የንግድ ማስታወቂያዎች አሁንም ድረስ በርካቶችን ማስደመማቸውን ቀጥለዋል።
የተለያዩ የንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎታቸውን ለተጠቃሚዎቻቸው ለማሳወቅ እና እንዲወደድ ለማደረግ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስገራሚ፣ግነት የበዛባቸው፣ፈገግታን የሚጭሩ ባስ ሲልም የሚያስደነግጡ ማስታወቂያዎችን ሲሰሩ እንመለከታለን።
ለዛሬም ያስገርማሉ ያልናቸውን የንግድ ተቋማት ማስታወቂያዎች በጥቂቱ ልናስቃኛችሁ ወደድን።
ይህ ምን የሚሉት እብደት ነው ሊሉ ይችላሉ ነገር ግን በአለም አቀፍ የቱሪዝም ማዕከሏ ዱባይ የተሰራ እውነተኛ ማስታወቂያ ነው።
የዓለማችን ትልቁ እና ስምንት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሜትር ከፍታ ባለው የቡርጃ ካሊፋ ህንጻ ጫፍ ላይ በኤምሬት የበረራ አስተናጋጅ ሰራተኛ የኤምሬት አየር መንገድ መልክቶችን ስታስመለክተን የሚያሳየን ነው። ይህ ማስታወቂያ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ እና ድንጋጤም የፈጠረም ነው።

በእዚህ የሚያህል ከፍታ ላይ ሆኖ ማስታወቂያ መስራት ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገመት ፈጽሞ አይከብድም። ሆኖም የበረራ አስተናጋጇ ግን ይህንን ማስታወቂያ ለመሰራት ለአንድ ሰአታት ያህል ቦታው ላይ ቆይታን አድርጋለች።የኤምሬት አየር መንገድም በዚህ ማስታወቂያ የሚሰጠው አገልግሎት ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ አገልግሎት እንዳለው ያስተዋወቀበት ነው።
ዶሪቶስ “አልትራሳውንድ” የተሰኘው ስያሜ የተሰጠው ይህ ማስታወቂያ አወዛጋቢ እና እጅጉኑ አስቂኝ መሆን የቻለ ነው።

ነገሩ ወዲህ ነው ዶሪቶስ የተሰኘው የቺፕስ ኩባንያ ምርቱን ለማስተዋወቅ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት የአልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ላይ ሳለች በማህጸኗ ያለው ጽንስ አባቱ የያዘውን የዶሪቶስ ቺፕ ለመወሰድ ሲሞክር የሚያስመለክት እንዲሆን ተደርጎ ተሰርቷል።በማህጸን ያለው ጽንስ ዶሪቶስን ለመያዝ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከህክምና ሰራተኞች አስገራሚ እና ያልተጠበቀ ምላሽ ፈጥሯል።
ምንም አይነት አደጋ ከፊቶ ቢደቀን እኛ እያለን ስጋት እንዳይገባዎት ይላል ይህ የኢንሹራንስ ኩባንያ በማስታወቂያ።ሴንትራአል ቢሄር የሚገኝ የኢንሹራንስ ኩባንያ ነው። ታዲያ ይህ ኩባንያ ደንበኞችን ለመሳብ የሰራው ማስታወቂያ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ እና ያነጋገረ አስቂኝ ማስታወቂያ መሆን ችሏል።
የባህል ህክምና ፍለጋ ወደ አንድ ህንጻ ያቀና ግለሰብ በአካባቢው በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሲደነግጥ እና ኩባንያው በብርሀን ፍጥነት ሲታደገው ያሳያል። ማስታወቂያውም በየትኛውም ችግር ውስጥ ሆነው ብቻ ወደ እኛ ይደውሉ ይላል።
ሴንትራአል ቢሄር የኢንሹራንስ ኩባንያ በኔዘርላንድ ከነበሩ የማይረሱ እና ውጤታማ የማስታወቂያ ስራ አንዱ መሆን የቻለ ነው።
ወጣትነቶን እና ጥንካሬዎን ወደነበረበት መመለስ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ የኤቪያን የተፈጥሮ ውሀ መጠጣት ግድ ይሎታል ይላል ማስታወቂያው። ይህ አይረሴ እና እውቅና ያገኘ የማዕድን ውሃ የማስታወቂያ ነው።
የጨቅላ ህፃናት ግድየለሽነት እንቅስቃሴ ዋናው የፈጠራ ፅንሰ-ሀሳብ ነበር።ማስታወቂያው ሰዎች በመስታወት ላይ ደስተኛ ሆነው የሚጨፍሩ ጨቅላ ህጻንነት ሲቀየሩ ያስመልክተናል።
ኢቪያን ከሌሎች የማዕድን ውሃ ብራንዶች ለመለየት እና ስሙን አዝናኝ የሆነ ምርት እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ማስታወቂያ ነው።
በ-ሀይማኖት ወርቁ












