፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 14 2016| NBC ETHIOPIA-መቆራረጥ መሰረዝ መደለዝ በሌለው እና ህይወት ባለው መልኩ ለተመልካቾች በቀጥታ ስርጭት በርካታ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ይተላለፋሉ፤
እያንዳንዱ ከእንቅስቀሴ፤ አለባበስ ፤ አነጋገር ጭምር ከፍተኛ ትኩረት መሳብ በመቻሉ የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞች እጅግ ጥንቃቄን የሚሹ መሆናቸውን ባለሞያቹ በተደጋጋሚ ያነሳሉ፤
አንዳንድ ጊዜ ግን በመዘናጋት አልያም ከሰዎች ቁጥጥር የሆኑ ሁነቶች ይፈጠሩ እና አስደንጋጭ፤ አሳዛኝ፤ አንዳንዴም ግርምትን ጫሪ እና አስቂኝ ሁነቶች በቴሌቭዢን የቀጥታ ፕርግራሞች ላይ እንመለከታለን፤
በተለይም የዕለት ዕለት ስራቸው የሆኑ የሚዲያ ባለሞያዎች እና ጋዜጠኞች በቀጥታ ስርጭት ለሚያጋጥሙ ሁነቶች በይበልጥ ቅርብ በመሆናቸው በተደጋጋሚ ለአስገራሚ ብሎም አስቂኝ ክስተቶቹ ሲጋለጡ እናስተውላለን፡፡
በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ የቃላት ስህተት፤ መውደቅ መናሳት፤ መሳቅ፤ የሚያወሩት ርዕሰ ጉዳይ መጥፋት፤ ሌላ ስራ ሲያከናውኑ ቀጥታ ስርጭት ላይ መግባት እና መሰል ሁነቶች በተደጋጋሚ ካየናቸው የቀጥታ ስርጭት አስቂኝ ክስተቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ለዛሬ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ካጋጠሙ በርካታ አስገራሚ ክስተቶች መካከል ጥቂቱን እናስቃኛችሁ፡-
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2010 ተዋቂው የቢቢስ ሪፖርተር ኩዊንቲን ሶመርቪል ያጋጠመው ክስተት እስካሁንም ድረስ የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ክስተቶች ሲነሳ በቀዳሚነት ከሚነሱ ሁነቶች መካከል አንዱ ነው፤

ጋዜጠኛው በሚያቀርባቸው የጦር ሜዳ ዘገባዎቹ እውቅናን ያተረፈ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነው፤ነገር ግን በአንድ ዕለት በአፍጋኒስታን በሚገኝ አንድ ስፍራ ከ 8 ቶን የሚበልጥ ሀሺሽ፤ኦፒየም፤ሄሮይንን የመሳሰሉ አደንዛዥ ዕፆች የያዘ ማሳ መገኘቱን እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ሀገራት መያዙን እና ማሳው እየተቃጠለ እንደሚገኝ ከጀርባው የሚነደውን እሳት እያመላከተ እየዘገበ ነበር፤ ነገር ግን ዘገባውን ከተወሰኑ ቃላት በላይ መቀጠል አልቻለም ነበር ከጀርባው የሚነዱት አደንዛዥ ጭሶች አማካኝነት ስራውን ፍጹም እረስቶት ወደ ካሜራ መሳቅ ሪፖርቱን አቋርጦታል፡፡
በማክሰኞ ማለዳ ዊል ሪቭ የተሰኘው የኤቢሲ ሪፖርተር ከቤቱ በመሆን የሰበሰባቸውን መረጃዎች በቀጥታ ስርጭት ከስቱዲዮ ላሉ ባልደረቦቹ እና ለተመልካቾች እያቀረበ ይገኛል፤ ከላይ ሱፉን ኮት እና ሸሚዙን በአግባቡ የለበሰው ሪፖርተሩ ባልደረቦቹም ሆነ ሌሎች ተመልካቾች ከስር በውስጥ ሱሪ ብቻ መልበሱን ግን ለደቂቃዎች አላስተዋሉም ነበር፤

ከላይ ሱፉን ኮት እና ሸሚዙን በአግባቡ የለበሰው ሪፖርተሩ ባልደረቦቹም ሆነ ሌሎች ተመልካቾች ከስር በውስጥ ሱሪ ብቻ መልበሱን ግን ለደቂቃዎች አላስተዋሉም ነበር፤ የካሜራ አንግሉ ሲቀየር እና በስክሪኑ ላይ ያለው ፅሁፍ ሲቀየር ግን ጋዤጠኛው ከስር በውስጥ ሱሪ ብቻ እንደሆነ በቀጥታ ስርጭት ታይቷል፡፡ በዚህም ጋዜጠኛው ለረዥም ቀናት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡
በሀገረ ቤልጂየም በቀጥታ ስርጭት ታዳሚያን እና እንግዶችን ይዞ የሚቀርብ የቴሌቪዥን ፕግራም አለ

በየጊዜው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ እንግዶችን እያመጣ የሚያናግረው ጋዜጠኛ ታዲያ በአንድ ዕለት በህክምና በተፈጠረ ስህተት አማካኝነት ለተለያየ አካል ጉዳት የተጋለጡ እንግዶችን አቅርቦ ማነጋገር ይጀምራል፡፡
ለአንደኛው እንግዳው ያቀረበላትን ጥያቄ መልሳ ከጨረሰች በኋላ፤ ሁለተኛው እንግዳ በተራው ምላሽ መስጠት ሲጀምር ግን በህክምና ስህተት አማካኝነት በተፈጠረበት የድምፅ መበላሸት አማካኝነት በሚያወጣው ቀጠን ያለ ድምፅ ሳቢያ ጋዜጠኛው ሳቁን መቆጣጠር አልቻለም፤ በዚህም ጋዜጠኛ ኤሪክ ከስራ ገበታው ቢሰናበትም የእርሱ የዛች ዕለት የቀጥታ ሳቅ ዛሬም ድረሰ አዝናኝ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
ፕሮፌሰር ሮበርት ኬሊ ይሰኛሉ ፤ እኚህ ግለሰብ በፈረንጆቹ 2017 በመጋቢት አንድ ቀትር ላይ በቢቢሲ የቀጥታ ስርጭት ዜና ተጋብዘው ቤታቸው በሚገኝ ቢሮ ውስጥ በመቀመጥ በደቡብ ኮሪያ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ አስተያየታቸውን እየሰጡ በሚገኙበት ሰአት ህጻን ሴት ልጃቸው እና የ 9 ወር ሴት ልጆቻቸው በመግባት የፈጸሙት ሁነት እና ወላጅ እናታቸው ይህንን ለመከላከል የሄዱበት ርቀት አስቂኝ ክስተትን በመፍጠር እንዲሁ ለረዥም ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ከመሆን ባለፈ የመንጊዜም አይረሴ የቲቪ የቀጥታ ክስተቶች መካከል ተካቷል፡፡

ክስተትን በመፍጠር እንዲሁ ለረዥም ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ከመሆን ባለፈ የመንጊዜም አይረሴ የቲቪ የቀጥታ ክስተቶች መካከል ተካቷል፡፡ መሰል አስቂኝ እና አስገራሚ የቀጥታ ስርጭት ክስተቶች በሀገራችን የቴሌቪዥን ስርጭቶች በተደጋጋሚ ተከስተው ቢያውቁም ሁነቱን ለታሪክ የማስቀመጥ እክል ምክንያት የውጩን ብቻ ተመልካች ሆነናል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












