፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 14 2016| NBC ETHIOPIA- የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) እየተሰጠ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስትና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ አዲስና ድጋሜ ለፈተና የሚቀመጡ 178,000 ተማሪዎች በጠቅላላ እንደሚፈተኑ ገልጿል፡፡
በ2015 ዓ.ም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠት የተጀመረው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና የዘንድሮውን ፈተና በዛሬው ዕለት በማኔጅመንት፣ ጂኦሎጂና ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እና ዲቨሎፕመንት ማኔጅመንት ተማሪዎች በመስጠት ተጀምሯል። ከዛሬ ሰኔ 14 እስከ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












