፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 13 2016| NBC ETHIOPIA-አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ህመም በቆዳ ላይ የሚወጣ ሽፍታ ያለው ሕመም ሲሆን ቫሪሴላ -ዞስተር (Varicella zoster) በሚባል ቫይረስ አማካኝነት ይከሠሰታል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ በዚህ በሽታ ይጠቃል፡፡ ይህ ሕህመም የሚከሠሰተው አስቀድሞ ጉድፍ (Chickenpox) በተያዙ ሰዎች ላይ ነው፡፡
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) እንዴት ይከሠሰታል?

ቫሪሴላ -ዞስተር ሰዎች በጉድፍ እንዲታመሙ የሚያደርግ ቫይረስ ሲሆን፤ ህመሙ ከአሳለፈ በኋላ ይህ ቫይረስ በአከርካሪ እና በአንጎል አቅራቢያ በሚገኙ ነርቮች ውስጥ ይቀመጣል። አመቺ ሁኔታን ሲያገኝ ይህ ቫይረስ በነርቮች ውስጥ በመጓዝ በቆዳችን ላይ አልማዝ ባለጭራ በሽታ እንዲከሠሰት ያደርጋል።
ለአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) አጋላጭ ምክንያቶች

????ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ ህመም
????የካንሰር በሽታ ወይም የኬሞቴራፒ ሕክምና
????አንዳንድ መድኃኒቶች (Steroids)
????ከፍተኛ ውጥረት ወይም ጭንቀት
የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ምልክቶች

????አልማዝ ባለጭራ ማንኛውንም የሰውነት ክፍል ሊያጠቃ ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን በአንድ ጎን በኩል በደረት፣ በሆድ ወይም በጀርባ ላይ ሲወጣ ይስተዋላል።
????ይህ ህመም ቆዳ ላይ ሽፍታ ከማሳየቱ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ የመደንዘዝ፣ የማቃጠል እና የማሳከክ ስሜት ይኖረዋል። ይህ ስሜት ከታየ 1 ወይም- 2 ቀናት በኋላ በአንድ የሰውነት ጎን ብቻ የቆዳ መቆጣት እና የቀበቶ ቅርፅ የመሰለ ዉሃ የቋጠረ፣ ሕህመም ያለው ሽፍታ መታየት ይጀምራል። ብዙ ጊዜ ሽፍታው ከጥቂት ቀናት በኋላ መድረቅ እና መክሰም ይጀምራል፡፡ ከዚያም በአንድ1 ወይም ሁለት2 ሳምንት ውስጥ ይጠፋል።
????በተጨማሪ ትኩሳት ፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና ህመሙ በተከሰተበት አካባቢ ንፍፊት (Lymphadenopathy) መውጣት ሊኖር ይችላል።
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ተላላፊ ነውን?

ታማሚዎች በቀጥታ አልማዝ ባለጭራን ማስተላለፍ አይችሉም። ነገር ግን የጉድፍ ክትባት ያልወሰደ ወይም ጉድፍ ታሞ የማያውቅ ሰው በታማሚው አካባቢ በሚሆንበት ጊዜ በጉድፍ በሽታ ሊጠቃ ይችላል።
ቫይረሱ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ ቀጥታ የቆዳ ንክኪ ወይም በትንፋሽ አማካኝነት ይተላለፋል። ስለዚህ የጉድፍ ክትባት ያልወሰደ ወይም ጭራሽ ታሞ የማያውቅ ሰው ከታማሚው ጋር የቅርብ ንክኪ ባያደርግ ይመረጣል።
የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ምርመራዎች ምንድን ናቸው?

የጤና ባለሙያዎች ሽፍታውን በማየት እና ስለምልክቶቹ በመጠየቅ ስለበሽታው መረዳት ይችላሉ። እንዲሁም ከሽፍታው ላይ ናሙና በመውሰድ ምርመራ ሊደረግ ይችላል።
የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ሕክምና
????በቤት ውስጥ የሚደረግ ሕክምና
????ሽፍታው የአለበትን አካባቢ ንጽሕፅህና መጠበቅ፣ በተጨማሪም እርጥበት እንዳይኖር በጥንቃቄ ማድረቅ
????ቆዳን የበለጠ ሊጎዱት ስለሚችሉል እርጥበት ያላቸውን ቅባቶች እና ክሬሞችን ማስወገድ
????የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ በቂ ዕረፍት ማድረግ
????ሰፋ ያሉ እና ምቾትን የሚሰጡ ልብሶችን መልበስ
????የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ፣ ውጥረትን መቀነስ
????በሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎች
????የፀረ -ቫይረስ መድኃኒቶች፤ ፣ እነዚህ መድኃኒቶች የቫይረሱን መራባት ለማገድ፣ የሕመሙን ክብደት እና ቆይታ ለመቀነስ እና ሽፍታው በፍጥነት እንዲድን ለማድረግ ያግዛሉ። በተለይም ሽፍታው በተከሠሰተ በ72 ሰዓአታት ውስጥ መወሰድ ከተጀመሩ ውጤታቸው ጥሩ ይሆናል።
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) መከላከያ መንገዶች
????ሕፃናት የጉድፍ መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ማድረግ
????በአደጉት አገራት ዕድሜያቸው ከ 50 በላይ ለሆኑ ሰዎች የአልማዝ ባለጭራ መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ይደረጋል።
????የአልማዝ ባለጭራ ታማሚ እስኪያገግምሙ ድረስ ርቀትን መጠበቅ ያስፈልጋል። በተለይም የጉድፍ ክትባትን ከአልወሰዱ ወይም በጉድፍ ተይዘው የማያውቁ ከሆነ ይህን ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል።












