፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ12 2016| NBC ETHIOPIA-የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለሁለተኛ ጊዜ ደቡብ አፍሪካን ለመመምራት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ አዲስ ዘመን ጀምራለች ብለዋል፡፡
ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ፓርቲያቸው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) የፓርላማውን አብላጫ ድምጽ ባለማግኘቱ ብቻውን መንግስት መመስረት ተስኖታል ፡፡
ይህን ተከትሎ ኤኤንሲ ከረጅም ጊዜ ተቀናቃኙ ዴሞክራቲክ አሊያንስ (ዲኤ) እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግስት ለመመስረት ስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል ፡፡
ራማፎሳ አዲሱን የጥምር መንግስት ምስረታ በመልካም ጎኑ ቢመለከቱትም እኩልነትን እስካላመጣ ድረስ ሀገሪቱ አለመረጋጋት ሊገጥማት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የ71 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች በሰጡት ድምፅ የሀገራቸው መሪዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸው ያላቸውን ተስፋ በግልፅ አሳይተዋል ብለዋል።
በፕሪቶሪያ በተደረገው ቃለ መሀላ የናይጀሪያውን ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኒቡን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው ፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












