፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA- በባህዳር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።በመርሃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማውና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አረጋ ከበደ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ የኮሪደር ልማቱ ከተሞች ለነዋሪዎች፣ ለጎብኚዎና እና ለሌሎች እንግዶች ምቹ የሚሆኑበት እድል የሚፈጥር ነው።
በአባይ ወንዝና የጣና ሃይቅ ዳር ላይ የተመሰረተችው ባህር ዳር ከተማ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች መሆኗ የኮሪደር ልማቱ የበለጠ ውብና ጽዱ እንድትሆን ያስችላታል ብለዋል።የኮሪደር ልማቱ 22 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እንደሆነ ተገልጿል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












