፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-ኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለግድቡ ግንባታ ላደረገው ሙያዊ አስተዋጽኦ “የላቀ ሙያዊ አስተዋጽኦ” በሚል ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
የናሽናል ሚዲያ አ.ማ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ዳኛቸው የእውቅና ምስክር ወረቀቱን ሲቀበሉ የሕዳሴው ግድብ በህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለ ብሔራዊ ፕሮጀክት ስለሆነ ሂደቱን በትኩረት ስንዘግብ ቆይተናል፤ለዚህም እውቅና መሰጠቱ የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የበለጠ እንድንሰራ ያግዘናል ብለዋል።

ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን በተጨማሪ ለግንባታው ከፍተኛ ሙያዊ አስተዋፅኦ አበርክተዋል የተባሉ መገናኛ ብዙሃን በየደረጃው የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












