፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 06 2016| NBC ETHIOPIA-
ታሪኮች በአግባቡ ተሰንደው አለመቀመጣቸው አጨቃጫቂ ትርክቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል ተባለ።
“በምክክር ትዳን ሀገር” ዘመቻ ሁለተኛ ምዕራፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን አለመግባባት ለመቅረፍ ያለመው ዘመቻው በሰሜን አሜሪካ ህጋዊ ሰውነት ባላቸው ፅናት ለኢትዮጵያ እና ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበራት የተዘጋጀ ነው።
በዛሬው በምክክር ትዳን ሀገር ዘመቻ ሁለተኛ ምዕራፍ የውይይት መድረክ ላይ በቀረቡ ጥናታዊ ፅሁፎች ታሪኮች በአግባቡ ተሰንደው አለመቀመጣቸው አጨቃጫቂ ትርክቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል።
በመሆኑም ሃገራዊ ምክክር እነኚህ ትርክቶች ላስከተሏቸው ችግሮች እልባት ለመስጠት ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል።
በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን የሚገልፁት ማህበራቱ ከወራት በፊት የመጀመሪያውን ዘመቻ አድርገው ነበር።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ዘመቻውን መቀላቀላቸውና ከፍተኛ ማህበራዊ መነቃቃት መፈጠሩ ተገልጿል።
በ-መቅደስ ደምስ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












