፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 05 2016| NBC ETHIOPIA- ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለሀጂ የጸሎት ስነ-ስርዓት መካ ገቡ፡፡
የሃጂን ስርዓት መፈጸም ከ5ቱ የእስልምና መሰረቶች ውስጥ አንደኛው ነው፡፡ የሳውዲ ባለስልጣናት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዓለም ዙሪያ ወደ መካ እስከ ማክሰኞ እለት መድረሳቸውን አሳውቀዋል፡፡
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከአርብ ጀምሮ በሚደረገው ሰነ-ስርዓት እንደሚሳተፉም ተነግሯል ፡፡

በዚህ ዓመት ለስነ ስርዓቱ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር ቀደም ሲል ከነበረው እንደሚልቅ ባለስልጣናቱ አሳውቋል፡፡
2019 ላይ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ወደ መካ ገብተው ነበር ሲል ለትውስታ የዘገበው ቲአርቲ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












