Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የነጻነት ፋና ወጊ_ሄርየት ታብማን

June 5, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 28 2016| NBC ETHIOPIA-ይህ የአፍሪካዊያንን አንገት ያስደፋ ፤ጠባሳው ዛሬም ድረስ ጨርሶ ያልሻረ የጨለማው ዘመን የወለደው የሲቃ ድምጽ ነው፡፡

በዚህ ጊዜ አፍሪካዊ ሆኖ መፈጠር ሃጥያት፣ስቃይ እና መከራ ነው፡፡በነጮቹ ዘንድ ከአፍሪካዊያን በተሻለ የቤት የተከበረ ነበረ፡፡ክቡሩ የሰው ልጅ እንደ ሙክት በግ ተሰልፎ ጨረታ የተደረገበት አሰቃቂ ዘመን ይሄኛው ለጉልበት ስራ ይሆናል!እቺኛዋ አርጅታለች፣ እየተባለ የሰው ልጅ እንደ ሸቀጥ የተቸበቸበበትና አትላንቲክ ባህርን ያቋረጥበት ታሪክ በማህደሩ የከተበው አሳፋሪ ክስተት ነው፡፡ ይህ ሁሉ በደል በሚፈፀምበት የጨለማ ወቅት ለብዙዎች ብርሃንን የፈነጠቀች አንዲት ሴት ተፈጠረች Harriet Tubman (ሄርየት ታብማን)”!

የተወለደችው እ.ኤ.አ በ 1822 በአሜሪካዋ “Maryland” ነው። ቤተሰቦቿ ባርያዎች ሲሆኑ ነጮቹ ገና በ 12 ዓመቷ የጥጥ እርሻ ውስጥ ቀኑን ሙሉ ጥጥ ሲያስለቅሟት ይውሉ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በአንዱ ባርያ የተበሳጨ ነጭ የወረወረው ከባድ ብረት ጭንቅላቷን መቷት ዕድሜ ልኳን ለከባድ ህመም እንድትጋለጥ ምክንያት ሆኗል፡፡

በወቅቱ በባሪያዎች በተለይም በሴት ባሪያዎች ላይ ይደርሱ የነበሩ በደሎች እጥፍ የደርሰባት ሄርየት እድሜዬን በሙሉ እንስሳ ሆኜ አልኖርም ብላ በመወሰን   እ.ኤ.አ በ1849  ወደ “Philadelphia” ጠፋች። የጠፋችው ግን ለማምለጥ ሳይሆን በህይወቷ ፈርዳ በባርነት የሚሰቃዩ ወገኖቿን ለማስመለጥ ነበር።

Portrait of activist and abolitionist Harriet Tubman, half length, 1895. Note: Image has been digitally colorized using a modern process. Colors may not be period-accurate. From the Gado Modern Color series. (Photo by Smith Collection/Gado/Getty Images)

ሄርየት ከ 1850 ጀምሮ ለተከታታይ አስራ ሶስት አመታት በድብቅ አሳቻ ሰዓቶችን እየጠበቀች ባርያ ሆና ትኖርበት ወደ ነበረው ቦታ በማምራት ከ 700 በላይ ባርያዎችን ማስመለጥ የቻለች የክፍለ ዘመኑ የነጻነት ፋና ወጊ ለመሆን በቃች፡፡እጅግ የሚደንቀው  ባርያዎቹን በምታስመልጥበት ወቅት አንዳንዶቹ ፈራ ተባ እያሉ አናመልጥም እያሉ ሲያስቸግሯት  ግንባራቸው ላይ “Revolver” ጥይት ደቅና ወደኃላ እንዳይመለሱ ታስፈራራቸው ጭምር ነበር።

ነጻ የወጡትንና በባርነት ሲማቅቁ የነበሩትን ወደ ሌላ ግዛቶች ወስዳ ስራ እንዲሰሩ እና እንዲቋቋሙም ማድረግ ችላለች፡፡ ይቺህ ጀግና ሴት የመፅሃፍ ቅዱሱ ሙሴ በግብፅ ባርነት የተያዙትን እስራኤላዊያንን ባህር ከፍሎ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር ከወሰደበት ታሪክ የማይተናነስ ተግባርን በመፈፀሟ “ሴቷ ሙሴ” የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቷት ነበር። “Harriet Tubman” ካስመለጠቻቸው ባርያዎች ውስጥ አንዱም አለመያዙ ታሪክ በማህደሩ ከትቦ ያስቀመጠው ጉዳይ ነው፡፡

“Harriet Tubman” ለሰራችው ስራ የተሰጣት የተለየ ገንዘብም ሆነ ስጦታ የለም! በመጨረሻም እጅግ በቆረቆዘ ደህንነት ውስጥ ኖራ በ 90 ዓመቷ እ.ኤ.አ 1913 ላይ አርፋለች!

ዛሬ ላይ “Harriet Tubman” ለከወነችው ድንቅ ተግባር መታሰብያነት ብዙ አደባባዮች እና ቤተ መፅሃፍቶች በስሟ ተሰይመዋል። ሃውልቶች ቆመውላታል። በታሪክም “ባርነትን ለማስወገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ዋና ዋና ግለሰቦች” መካከል አንዷ ሆና ሰፍራለች!

እ.ኤ.አ 2016 ላይ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት “Barack Obama” የአሜሪካ 20 ዶላር ላይ ያለው 7ተኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የነበረው “Andrew Jackson”ተነስቶ የ “Harriet Tubman” ፎቶ ሃገሪቱ 20 ዶላር ኖት ላይ እንዲታተም ውሳኔ አስተላልፎ ነበር! ነገር ግን ሂደቱ ሳይቋጭ “Obama” ስልጣን በመልቀቁ ይህ ውጥን በዕቅድ ቀርቷል፡፡ 

በ-ፀጋሁን አሰፋ

ShareTweetShare
Previous Post

በህንድ የተከሰተው ከፍተኛ ሙቀት

Next Post

በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?

በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?

በ 2024 ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገቡ መፅሀፍት

በ 2024 ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገቡ መፅሀፍት

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የደህንነትና የጥራት መስፈርቶችን ያላሟሉ የወተት ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የደህንነትና የጥራት መስፈርቶችን ያላሟሉ የወተት ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?